Thursday, September 19, 2013

አዳፍኔ ለመተኮስ የ “iPad” ዕገዛ


iPad to fire
ከአንድ መቶ ሺ በላይ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውና እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነው የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት የአማጺያኑ ኃይል ከሚጠቀመው ቤት ሰራሽ መሣሪያዎች ሌላ የቴክኖሎጂ እሴቶችን በመቀላቀል የሚጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የሬውተር ዘጋቢ የሆነው መሐመድ አብደላ ባነሳው በዚህ ፎቶ ላይ እንደሚታየው የነጻ ሶሪያ ሠራዊት አማጺያን ከደማስቆ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አዳፍኔ ለመተኮስ በ iPad ሲታገዙ ይታያል፡፡
የጦር መሣሪያ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ አማጺያኑ በፎቶግራፉ ላይ እንደሚታየው በቴክኖሎጂ ቢታገዙም የመተኮሻው ቱቦ አቅጣጫና አቀማመጥ በጣም በቅርብ በሚገኝ ዒላማ ለመምታት አስበው ካልሆነ በስተቀር አዳፍኔውን የሚተኩሱት ራሳቸውን ለማጥፋት ይመስላል፡፡
በምስሉ እንደሚታየው አማጺያኑ በጉዳዩ የረቀቁበት ቢመስልም አነጣጠራቸውና አተኳኮሳቸው “ቦምብ ጥሎ የመጸለይ” ዓይነት ይመስላል በማለት በጉዳዩ ላይ ዕውቀት ያላቸው የጦር መሣሪያ ባለሙያ በምጸት ለሬውተርስ ተናግረዋል፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)
(ፎቶ፡ በነጻ ሶሪያ ሠራዊት ሥር የአሱድ አላህ ብርጌድ አካል የሆነው የአንሳር ዲማክ ብርጌድ አባላት “iPad” በመጠቀም ደማስቆ፤ ጆባር አካባቢ ቤት ሰራሽ አዳፍኔ ሲተኩሱ፤ መስከረም 5፤2006፡፡ ሬውተርስ)

No comments:

Post a Comment