ኃይለማርያም ደሣለኝ አይሲሲን የተመድ ጉባዔ ላይ አጥላሉ
ኃይለማርያም ደሣለኝ አይሲሲን የተመድ ላይ አጥላሉ
የአፍሪካ ትንሣዔ ሩቅ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 68ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩና መገለጫው ሲሉ የመዋጋትን አስፈላጊነት ቅድሚያ ሰጥተው አመልክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የአህጉሪቱን ችግሮችና ስኬቶች ያሏቸውን አብራርተው በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት ላይ ያላቸውን ቅሬታም አሰምተዋል፡፡
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረትንም ወክለው መሆኑን በንግግራቸው ላይ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የኢትዮጵያን ጉዳይ በንግግራቸው ላይ አላነሱም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማርገብ የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እንደሚፈትሹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ተናግረዋል፡፡
ሶሪያ ኬሚካል የጦር መሣሪያዎቿን እንድታስወግድ ለሚያስገድዳት ስምምነት ባትገዛ ቀጭ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኒኩሌር መርኃግብሯ ላይ ጠንካራ ድርድሮችን ለማድረግ ሃገራቸው ዝግጁ መሆኗን አዲሱ የኢራን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮውሃኒ አስታውቀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

No comments:
Post a Comment