Wednesday, September 25, 2013

(ሰበር ዜና) ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ፎቶ አንሺ ተፈቱ

(ሰበር ዜና) ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ፎቶ አንሺ ተፈቱ

ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀ መንበር
(ዘ-ሐበሻ) ከሰዓታት በፊት ዘ-ሐበሻ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “አባሎቻችንን ካልፈታችሁ እኔማ አብሬ እታሰራለሁ” በሚል መታሰራቸውን መዘገቧ የሚታወስ ነው። አሁን ከአዲስ አበባ ከዘ-ሐበሻ በደረሰው ሰበር ዜና ዶ/ር ነጋሶ ለ4 ሰዓታት ከቆዩ በኋላ ተፈተዋል።
የፊታችን እሁድ በመስቀል አደባባይ አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ቅሰቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት መታሰራቸውን ተከትሎ እነርሱን ለማስፈታት ወደ ሽሮሜዳ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ያመሩት ዶ/ር ነጋሶ “እነዚህን ልጆች የላኳቸው እኔ ነኝ፤ እነርሱን ከምታስሩ እኔን እሰሩኝ በማለታቸው የተወሰኑት ልጆች መፈታታቸውና አንዱ ካሜራ አንሺን ፖሊስ አልፈታም በማለቱ ዶ/ር ነጋሶም እርሱ ካልተፈታ አብሬ እታሰራለሁ በሚል ከፖሊስ ጣቢያ አልወጣም በሚል መቆየታቸውን ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ዘግባ ነበር። አሁን በደረሰን ሰበር ዜና ዶ/ር ነጋሶና የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ካሜራ አንሺ ለ4 ሰዓታት ከታሰሩበት ተለቀዋል። ዘ-ሐበሻ እርሳቸውን አግኝታ ለማነጋገር ጥረት እያደረገች ነው። ይመለሱና ይጎብኙን።

No comments:

Post a Comment