https://www.youtube.com/watch?v=4scyf86MTCs
አሳዛኝ ሰበር ዜና « ህይወት እንደዋዛ » ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።
አሳዛኝ ሰበር ዜና « ህይወት እንደዋዛ »
ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት
ቀን መስከረም 8 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እንምባ ሲያራጭ፡ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንተራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል።
የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር ፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ በተከታታይ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህልፈተ ህይወት መሰማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደንግጦል።
በተለይ ትላንት ማለዳ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከጠዋቱ 3 አካባቢ አስከሬንዋ ጊዘያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ፡ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ህመሙ አገርሽቶባት ስታቃስት «ጣረሞት ስታሰማ» ፡ እንደ ነበር የሚናገሩ ወገኖች ዲፕሎማቱ ትብብር እንዲያደርጉላት ስልክ ቢደወልላቸውም በወቅቱ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወጣቷ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉን ይገልጻሉ።
ሞች እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዲፕሎማቱ በኤንባሲው ሃላፊነት ወደ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመር እና ህይወቷን ከሞት መታደግ ሲችሉ ባስዩት ግዴለሽነት እና ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው አሰራር የወጣቷ ህይወት እዚህ በረሃ ላይ ቀርቷል ብለዋል። ወጣቷን ወደዚህ ግዜያዊ መጠለያ ግቢ ዲፕሎማቱ ከአሰሪዎቾ ተረክበው ሲያመጧት ሃኪም ቤት ውሰዱኝ ህይወቴን አጣሁ !! አድኑኝ ኸረ የወገን ያለህ !! ኸረ ያህገር ያለህ !! አናቴ ድረሺልኝ !! እያለች ትማጸናቸው እንደነበረ በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል ። የወጣቷ የሰውነት አቋም እና አጠቃላይ ሁኔታ ያዩ አንዳንድ ታዛቢዎች በውስጦ፡የቆየ በሽታ እንደሌለባት እና ወጣቷ አንጀቴ ተቃጠለ ውሃ ውሃ ስትል እንደነበር እና ሃኪም ቤት ውሰዱኝ፡እያለች ልብ በሚነካ ሁኔታ ስትማፀን የታዘቡ ወገኖች ምናልባትም ከምግብ ጋር የተቀልላቀለ መርዝ ነክ ነገር በልታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ያጎላሉ። በማያያዝ ዲፕሎማቱ ወጣቷን ከአሰሪዎቾ ተቀበለው ወደ መጠለያ ሲያመጧት ለአመታት የደከመኩበትን የወር ደሞዜን እባካቹ ከአስሪዪ ላይ ተቀበሉልኝ እያለች ትጮህ እንደ ነበረ እና ወደ መጨረሻ አካባቢ እየደከመች ስትመጣ ሞች በሚያሳዝን አንደበት ሆስፒታል በር ላይ ወስዳችሁ ጣሉኝ፡የወግን ያለህ እያለች እስከ ዕለት ሞቷ ታለቅስ እንደ ነበረ እና ይህንንም ተማጽኖ ዲፕሎማቶቹ «የመንፈስ ጭንቀት ነው» ፡ «ስራ በዝቷባት ነው» ፡« ሃገር መግባት ፈልጋ ነው» ስታጭበረብር ነው» ወዘተ …… በሚል ፌዝ በጭካኔ ሌሎችን ሰላም ትነሳለች በሚል ለብቸዋ ኮንቴነር ውስጥ፡አስገብተው እንደቆለፉባት እና በነጋታው ወጣቷ ሞታ ማደሯን አንዳንድ የኮሚኒቲው አባላት እንባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ ትላንት 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ አካባቢ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ የወጣቷ አስከሬን በሳውዲ የማዘጋጃ ሰራተኞች ተነስቶ ወደ አልታወቀ ስፈራ እንደተወሰደ እነዚህ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ
No comments:
Post a Comment