Friday, September 27, 2013

የአንድነት አመራር አባላት ጊዜያዊ እገታ(DW)

የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ዓመራር አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ኣበባ ላይ ለጠሩት ሰልፍ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዳልቻሉ ኣስታወቁ በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ የፓርቲው ዓመራሮች ዛሬ ለተወሰኑ ሳዓታት በፓሊሶች ታግተው መለቀቃቸውን ፓርቲው ኣስታውቋል

የፓርቲው ሊቀመንበር / ነጋሶ ዲዳዳም ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ ሁኔታ ታግተው መለቀቃቸው ይታወሳል በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እና የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ ከፍተና ዓመራር አቶ ግርማ ሰይፉ ዛሬ ከታገቱበት የአራዳ /ከተማ ፓሊሲ መምርያ ሆነው በእልክ ለዶቸቤሌ እንደገለጹት እሳቸውን ጨምሮ ኣጠቃላይ የፓርቲው ዓመራሮች እና ለቅስቀሳየተሰማሩ አባላቱ ባይታሰሩም በእሳቸው ኣባባል ታግተዋል አቶ ግርማ እንደሚሉት በኣሰራር ሰላማዊ ሰልፉ ተከልክለዋል በሰበብ ኣስባቡ ሌላ ጊዜ ሌላ ቦታ እየተባለ ግን ይነገራቸዋል ምክኒያታቸው ደግሞ የቅስቀሳ ፈቃድ የላችሁም የሚል ነው የቅስቀሳ ፈቃድ በራሱ ህገ ወጥ ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰይፉ ፈቃዱንም ለማምጣት ፈቃድ ሰጪውም ሆነ የሚሰጥበት ቦታም ኣይታወቅም ብለዋል።
ይሁን እንጂ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑንም ሆነ የፓርቲውን ዓመራሮች ከማዋከብ ኣልታቀበም ያለመያዝ መብት ያላቸው አቶ ግርማ ሰይፉም ጭምር ከእገታውኣላመለጡም አቶ ግርማ እንደሚሉት ኣሁን የተያዘው ነገር እገታ ነው እሰሩን ብንልም ፈቃደና ኣይደሉም የሚሉት አቶ ግርማ ለጊዜው ቡድኑን በማገት እንቅስቃሴውን ማስተጎጎል ነው የተፈለገው ብለዋል በኣጠቃላይ ይላሉ አቶ ግርማ ሰይፉ የዚህ ዓይነቱ ኣሰራር በሰላማዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱት ኃይሎች በር እየዘጋ በህገ ወጥ መንገድ ለመታገል ለመረጡ ቡድኖች ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነውድምጽ አምስት አቶ ግርማ ሰይፉ በአቶ ግርማ ሰይፉ መግለጫ መሰረት ዛሬ ከቀትር በኃላ በሶስት ተሽከርካሪዎች አማካይነት የተሰማራው የቅስቀሳ ቡድን ታግቶ ቅስቀሳውም ተጨናግፈዋል ዓላማውም ሰላማዊ ሰልፉን ማሰናከል ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰልፉን በተመለከተ ኣመራሩ ተሰብስቦ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ ኣስታውቀዋል ይህንኑ ኣስመልክተው የበኩላቸውን ምላሽ እንዲሰጡን የኣራዳ /ከተማ ፖሊስ መምሪያን በስልክ ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ኣልተሳካም
ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ
AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

·        ቀን 27.09.2013

No comments:

Post a Comment