Monday, September 9, 2013

ይህ ቀልድ ለወያኔ ወይም ለኢሀዲግ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር፤ ጭንቅላታቸዉ እንዲሰራ ይሆን ነበር

=ቀልድ=
በአሜሪካ ሀገር አቋራጭ ባቡር ውስጥ ነው። አንድ ወጣት የአሳ ጥብስ መብላት አማረውና አስተናጋጅቱን “ሶስት አሳ በጥሩ ሁኔታ ጠብሰሽ አምጪልኝ” በማለት አዘዛት። አስተናጋጇም በትዕዛዙ መሰረት አሳዎቹን አመጣችለት። ወጣቱም መብላት ጀመረ። ሆኖም አሳዎቹን ሲበላ ራስ ራሳቸውን ከሰውነታቸው እየገነጠለ ከሳህኑ ላይ ያስቀምጥ ነበር። ይህን ያየ ተመልካች “የአሳ ራስም ይበላል እኮ! ለምንድነው ራስ ራሱን የማትበላው?” በማለት ጠየቀው።
“ አይ ራሱን እሸጠዋለሁ”
“ለማን ነው የምትሸጠው?” 
“ጭንቅላታቸው ለማይሰራ”
“ጭንቅላት ያሰራል ማለት ነው?”
“በደንብ ነው እንጂ!”
“ታዲያ ስንት ነው የሚሸጠው?”
“የአንዱ ራስ ዋጋ ሁለት ዶላር ነው”
ሰውዬው ገረመውና እያንዳንዱን ራስ በሁለት ዶላር ሂሳብ ገዛቸው። የአሳዎቹን ራስ በልቶ ካጣጣማቸው በኋላም “በጣም ጣፋጭ ነገር ነው። ለመሆኑ አሳዎቹን ስንት ገዝተሃቸው ነው?” በማለት ወጣቱን ጠየቀው።
“እያንዳንዱን በአንድ ዶላር ሂሳብ”
“አንተ ወሮ በላ! ሙሉውን ዓሳ በአንድ ዶላር ገዝተህ ነው እንዴ ጭንቅላቱን ብቻ በሁለት ዶላር የምትሸጥልኝ?”
ወጣቱ ታዲያ እየሳቀ “ዋው! አላልኩህም? ጭንላትህን በደንብ አሰርቶታል ማለት ነው” በማለት መለሰለት።

No comments:

Post a Comment