Sunday, November 10, 2013

"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት

(by:Mesfin)
በሪያድ የዛረው ሰልፍ የሚመጣውን አደጋ በመፍራት ተበትኗል::
"ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን"የሳኡዲ ባለስልጣናት


አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲ ጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ እንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት እና የቆንስላው ዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተት መስመር ሊይዝ አልፈለገም:: እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናት አነጋገው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ 40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል::

በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸው ተሰማ። እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ መሰረት በሰልፈኞች በተወረወሩ ድንጋዮች አንድ የሳውዲ ዜጋ መሞቱንም ዘግቧል።

እነዚሁ በነዋሪዎች ድብደባና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወደ ሪያድ ኢምባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪና እንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።

3 comments:

  1. I don't think that the government of Ethiopia would reconcile the difference for the benefit of the people (remind what Kemal said earlier and the bitter banning beating and torture to the demonstrators in front of Saudi Embassy in Eth). Rather, I do believe that EPRDF initiated this and requested the Saudi to expel Ethiopians to get a relief from its political problems. If Muslims expelled from Saudi, that means (to the calculation of woyane), they will concentrate on resolving problems in Eth and live as of the order and anarchy of Woyane. It is to force the muslim community to hate the Arab world and depend heavenly on Woyane. How long they keep cheating the Ethiopian people like this? The people of Ethiopia need to show bitter consequences in addition to longer silence (which by itself is great).

    Minasie Gessesse

    ReplyDelete
  2. የእምቢታ ሰራዊት
    የነጻንት አዉሎ ንፋስ፤
    ዳዊት ጎልያድን ያንጋለለዉ አንድ ጠጠር ድንጋይ በወንጪፍ ወርውሮ ግንባሩን መቶ ነው፤ አንዱን ትልቅ ተራራ አንድ ትንሽ ወንዝ ሸርሽሮ ያፈርሰዋል፤ ስለዚህ የነጻነት ትግል በልዩ ልዩ ዘዴ የሚክናወን ሲሆን ዋና መሳርያዉ የሰፊዉ ህዝብ ትብብር ነው።
    ፩. ሰላማዊ ሰልፍ በተወሠነ ቦታ ብⶫ መሆን የለበትም፤ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሁኖ በተⶫለ መጥን ትቀነባብሮ በየከተማዉ በየመንደሩ በየቀብሌዉ በየሰፈሩ ቢደረግ ለመቆጣጠር አይቻልም፤ በሚልዮን የሚቆጠር ሰራዊት ማዓበል ይሆናል፤ ይሔም ተከታትሎ ያለረፍት በየቀኑ መደረግ አለበት።
    ፪. የሕዝብን መብትና ነጻነት፤ ሃብቱንና መሬቱን፤ ሞያዉንና ምግባሩን፤ የዓልት እንጀራዉን የሚነሱ፤ ዜግነቱን የሚያሳጡ፤ ከኑሮ ቦታዉ የሚፈነቅሉ፤ ማናቸዉም ድንግጋትና አዋጆች ድርጊቶች በእምቢታ መቃወም፤ ማሰናከል፤ ማፍረስ፤ እንደዚህ ያለ ድርጊት የትም ቦታ በማንም ወገን ላይ ሲፋጸም በአንድነትና ብሕብረት መቃወም። የእምቢታ ሰራዊት ገንቢ ምሆን።
    ፫. እያንዳንዱ ዜጋ፤ እያንዳንዱ ሕብረሰብ፤ እያንዳንዱ ባለሞያ፤ ይህ የራሴ ጉዳይ ነው፣ ያገሬ ጉዳይ ነው ብሎ በንጹህ ልቦና ይሄንን ትግባር ከፈጸም፣ ማንም ምንም ሊያቆምው የማይችል የነጻነት አዉሎ ንፋስ ተነሳ ማለት ነው፤ ዉጤቱም የማያጠራር ነዉ። ያለ ትግል ያለ ምስዋትነት የሚገኝ ነጻነት የለም።
    ችርነቱ ያማያልቅ አምላክ ምህረቱን ይስጥን።
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
    እመሩ ዘለቀ
    መስከረም ፪፻፮ ዓም
    ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
    September 23, 2013
    አምባሳደር እምሩ ዘለቀ

    ReplyDelete
  3. ቅድሚያ ወያኔን ነው!!
    ደላላው ወያኔ ለዐረብ አሸሻጩ፣
    ገጠር ድረስ ሄዶ ትዳር እያፋቱ - እርስ በርስ እያጋጩ፣
    አዲስ ጎጆ አፍርሶ "ሀ" ብሎ ከንጭጩ::
    በቀቢጠ ተስፋ ልብን አንጠልጥሎ፣
    የራበውን አንጀት በመና ደልሎ፣
    ለዐረብ ዳረጋቸው ጉቦ ተቀብሎ::
    በዐረብ ሰላጤ ብሎም በቀይ-ባሕር፣
    በሲና በረሃ በጭካኔ ምድር፣
    የገጠር ሙሽራ ሴት ወንድ አልቀረ፣
    ተማሪው ምሩቁ የተመራመረ፣
    ያልፍልኛል ብሎ ስንቱ ወጦ የቀረ::
    ዐረብ ግፍ አይፈራ ስብዕና የለው - - - ጭራሽ አረመኔ፣
    ስንቱን ከፎቅ ጥለው ገሎ በጭካኔ፣
    ስንቱን እህል ነፍገው ገደሉ በጠኔ፣
    እግዜር ይክተታቸው ከሲዖል ኩነኔ::
    ተልዕኮው ቀላል ነው ብዙም ሚስጢር የለው፣
    ይህም ዘዴ ሆኖ ያው እንደልማዱ ትውልድ/ዘር ማጥፋቱ ነው፣
    ለዚህ እርኩስ ስራው ጥማድ በሬ አይበቃው - - - ተመኑ ብዙ ነው፣
    ከዚህም ለመላኪያ ከዚያም ለአባይ ግድብ የሚሞጨልፈው፣
    ወገኔ ተረዳ መንታ መንገዱን ተው፣
    የዐረብ ጠላትነት (በሶማሌ ወጉን) ከጥንትም ያለ ነው፣
    ከአገር ነቅሎ መጣል የባንዳን ጥርቅም ቅድሚያ ወያኔን ነው (2)!!
    አንተነህ ሽፈራው/23 Nov 2013
    መታሰቢያነቷ በዐረብ አገር በግፍ ለተገደሉ፣
    ክብራቸው በተለያዩ መንገዶች ለተደፈሩና
    አሁንም ለሚንገላቱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ
    ትሁንልኝ!!

    ReplyDelete