Wednesday, November 6, 2013

ዋልያ ወደ ጆርዳን …..ቀኑ ተቀየረ!!”…ካልታዘልኩ አላምንም” አለች ሙሽሪት



ዛሬ ሰርግሽ ነዉ አልዋት፤እናም ጭፈራዉ ደራ…እንግዶቹም ከየቦታቸዉ መጡ፣ግን ዋናዉ ሰዉ ቀረ..ሙሽራዉ ሊከሰት አልቻለም፤ይህ ነገር ሙሽሪትን አሳዘናት፤2ተኛ ጊዜም ሰርግ ተደግሶ አሁንም ሙሽራዉ ቀረ፤3ተኛም ተሰለሰ፤ከዚህ ወዲህ የሰርግሽ ቀን ነዉ ብላችሁ እንዳትነግሩኝ አለች ሙሽሪት….’’አዝሎ ካልወሰደኝ በፍጹም አላምንም” አለቻቸዉ!!
የዋልያዉ ወዳጅነት ጨዋታ ጉዳይም ካልታዘልኩ አላምንም እንዳለችዉ ሙሽሪት ነገር ሁንዋል፤መጣ ሲባል ይቀራል፤ይሄዳሉ ሲባል ይተዋል፤ብቻ ምን አለፋቸሁ…ጋና..ካሜሮን..ቡርኪናፋሶ..ሴራሊዮን..እያለ እያለ 10የሚደርሱ ሀገራት ስም ከዋልያዉ ወዳጅነት ጨዋታ ጋር ተያይዝዋል፤
ኢራቅ አዲሱ የወዳጅነት የሚያደርግ ቡድን ተብሎ ትናንት በሚስጥር እንደተነገራቸዉ ነግሬያችሁ ነበር፤ሌሊቱን ደግሞ ዛሬ ማለዳ ላይ ወደ ጆርዳን ይኬዳል የተበላዉ ወደ ነገ እንደዞረ ታዉቅዋል፤በዱባይ በኩል ነበር ዩርዳኖስ የሚሄዱት …ነገር ግን ለምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት የመሄጃ ቀኑ ነገ ሁንዋል፤አርብ የጨዋታዉ ቀን ነዉ፤ቅዳሜ ደግሞ ተመልሰዉ ይመጣሉ፤ከዛም የነገ ሳምንት ሀሙስ ወደማይቀርበት ካላባር ያመራሉ፤
ዋልያዉ ነገ ይሄዳል ተባለ እንጂ ሊቀርም ይችላል፤አሁን ሁሉም ሰዉ ማረጋገጥ የሚፈልገዉ ነገር አለ፤የናይጄሪያዉም ጨዋታ ቀረ እንዳይባል ስጋት ዉስጥ የገባበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ:: አዳዲስ ነገሮችን ሚስጥርም ቢሆኑ አካፍላችሁዋለሁ!!መልካም ቀን!!
via http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment