Saturday, November 9, 2013

ሃይለማርያም ቤተ መንግስቱ አስጠልቶታል::የሕወሓቱ ቴዎድሮስ ሃጎስ ሃይለማርያም ደሳለኝን ይተካሉ ተብለው ይጠበቃል::ቴዎድሮስ አድሃኖምስ?


ምንሊክ ሳልሳዊ:-በሁለቱ የሕወሓት አንጃዎች መካከል የተነሳውን አለመግባባት በእርቅ ለመፍታት የሚደረጉ የውስጥ ጥረቶች እንደቀጠሉ ሆነው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሕወሓት ከእጄ ወጣ የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ከሃይለማርያም በመረከብ በበላይነት ለመቆጣጠር ጉዞውን ቀጥሏል:: ከነቤተሰባቸው የምንሊክ ቤተመንግስት ያስጠላቸው እና የሰለቻቸው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ዘመናቸው ማዘዝ የማይችሉ የተባሉትን እንደ በቀቀን የሚደግሙ ከመሆናቸውም በላይ በመኝታ ቤታቸው ሳይቀር የድምጽ መቅጃ መሳሪያ ተተክሎባቸው እንደነበር በገሃድ ታይቷል:: ምንም አይነት ስልጣን ሳይኖራቸው የስልጣን ጊዜያቸውን የሚያገባድዱት ሃይለማርያም በሳቸው ዘመን በሟች መለስ ዜናዊ ጊዜ ታይቶ የማይታወቅ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የሙስና መስፋፋት እና የኢኮኖሚ እድገት መላሸቅ በይፋ ትንንሽ አስተዳዳሪ ያሌላቸው አዛዥ መንግስታት መፈጠር የኢኮኖሚ ዘረፋ ማካሄድ በስፋት ተስተውሏል::
የስብሃት ነጋ ቡድን የበላይነቱን የያዘው የሕወሓት አመራር የአባይ ወልዱን እና የባልደረቦቹን ቡድን በማንበርከክ ላይ ያለ መሆኑ የተረዱት በመሆኑ ከመውደቅ ለመዳን የተሰነጣጠቀውንም ሕወሓት ለመጠገን ሲባል የአባይ ወልዱ ቡድን ወደ ስብሃት ነጋ እያዘነበለ መሆኑ ታውቋል:; ይህንን ተከትሎ ምንጮች ለኢትዮጵያ ሪቭው እንደጠቆሙት አይቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ ሕወሓትን በሊቀመንበርነት ኢትዮጵያንም በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲያስተዳድሩ ታጭተዋል:: ሆኖም ግና የስብሃት ነጋ ቡድን እስካሁን እያደእረገው ዘመቻ የሚጠቁመው ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ተቅላይ ሚኒስትርነት ለማምጣት ሲሆን በዚህም ሃይለማርያም ደሳለግን ከ 2008 ጀምሮ እንደማይኖር የወሰኑበት መሆኑ ታውቋል::


Via:-http://www.ethiopianreview.us/49841

No comments:

Post a Comment