Wednesday, November 6, 2013

«የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር መግለጫዎችን ማውጣት ብቻ በቂ አይደለም»

 by  0

ሚስተር አማዱ ማህታር ባ፣ የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ምንም እንኳን የፕሬስ ነፃነትና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ለማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በተለይ ለማደግ ጥረት በምታደርገው አፍሪካ እጅግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም፣
ይህን ማሳካት የሚቻለው ግን ዋሽንግተን፣ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ፣ ዳካር ወይም ሌላ ቦታ ተቀምጦ መግለጫዎችን በማውጣት እንደልሆነ የአፍሪካ ሚዲያ ኢንሼቲቭ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር አማዱ ማህታር ባ ገለጹ፡፡
ሥራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት ዛሬ በአዲስ አበባ የሚከፈተውን ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረምን አስመልክቶ አዘጋጆቹ ማክሰኞ በሰጡት የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ የአፍሪካ የፕሬስ ነፃነትና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሊሳካ የሚችለው ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ውሳኔ ሰጪ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት መሆን እንዳለበትም አክለው አስረድተዋል፡፡
“በአፍሪካ የሚዲያ መልከ አምድር ላይ በርካታ ወትዋች ድርጅቶች አሉ፡፡ እኛም ለአፍሪካ የፕሬስ ነፃነት ከሚወተውቱ ተቋማት መካከል አንዱ ነን፡፡ ነገር ግን የእኛ መንገድ ከሌሎቹ የተለየ ነው፤

No comments:

Post a Comment