Friday, September 20, 2013

የኤርትራ መንግሥት የዛሬ 12 ዓመት ካሠራቸው አሥራ አንድ ባለሥልጣናት በሕይወት የሚገኙት ሁለት ብቻ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል

ቪኦኤ ዜና ዋሺንግተን ዲ.ሲ.

በዚህ የቡድን ፎቶግራፍ ውስጥ ከታሠሩት አምስቱን ታገኛላችሁ፤ የቆሙት፡- ዑቕባ አብረሃ፣ ዓሊ ሰዒድ አብደላ፣ ስብሃት ኤፍሬም፣ ኃይሌ ወልደትንሣዔ፣ ጴጥሮስ ሰሎሞን፣ ሞሐመድ ሰዒድ በረኽ፣ መስፍን ሐጎስ፣ አል-አሚን ሞሐመድ ሰዒድ፤ የተቀመጡት፡- ብርሃኔ ገብረእግዚአብሔር፣ ኢብራሂም አፋ፣ ሮማዳን ሞሐመድ ኑር፣ ኢሣይያስ አፈወርቂ፣ ማኅሙድ
የኤርትራ መንግሥት የዛሬ 12 ዓመት ካሠራቸው አሥራ አንድ ባለሥልጣናት በሕይወት የሚገኙት ሁለት ብቻ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ፓርላማዎች አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡
የኤርትራ መንግሥት የዛሬ 12 ዓመት ካሠራቸው አሥራ አንድ ባለሥልጣናት በሕይወት የሚገኙት ሁለት ብቻ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ፓርላማዎች አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡
ቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጴጥሮስ ሰሎሞን እና ከኃይሌ ወልደትንሣዔ በስተቀር ሁሉም በሕይወት ላይኖሩ እንደሚችሉ የዓለም ፓርላማዎች ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች መርኃግብር ኃላፊ ሮዤ ሁዪዜንጋ ገልፀዋል፡፡
ቀድሞ የኤርትራ ብሔራዊ ሸንጎ አባላትና የመንግሥት ባለሥልጣናትም የነበሩት ዑቕባ አብረሃ፣ አስቴር ፍስሃፅዮን፣ ብርሃኔ ገብረእግዚአብሔር፣ ባራኺ ገብረሥላሴ፣ ሃማድ ሃሚድ ሃማድ፣ ሳለህ ኬኪያ፣ ጀርማኖ ናቲ፣ እስጢፋኖስ ስዩም፣ ማኅሙድ አሕመድ ሸሪፎ፣ ጴጥሮስ ሰሎሞን፤ ኃይሌ ወልደትንሣዔ ተይዘው የታሠሩት የዛሬ 12 ዓመት መስከረም 8 / 1994 ዓ/ም ነበር፡፡
ባለሥልጣናቱ የተሠሩት ዴሞክራሲያዊ ለውጦችና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ለፕሬዚዳንቱ ግልፅ ደብዳቤ በፃፉ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደነበረ ያስታወሱት የኅብረቱ ባለሥልጣን ከዚያ ወዲህ አንድም ጊዜ ጉዳያቸው ለፍርድ መቅረቡን እንደማያውቁ ሚስተር ሁዪዜንጋ ገልፀዋል፡፡
የዓለም ፓርላማዎች ኅብረት – አይፒዩ የሰዎቹን ጉዳይ እጥብቆ የያዘው መሆኑንና በብርቱም የሚከታተለው ከባድ ጉዳይ መሆኑን ሚስተር ሁዪዜንጋ አመልክተው ኅብረታቸው በኤርትራ መንግሥት ላይ ጫና ማሣደሩን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
የዓለም ፓርላማዎች ኅብረት 162 አባል ፓርላማዎች ያሉት ዓለምአቀፍ ተቋም ነው፡፡
የትግርኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረባ ተወልደ ወልደገብርዔል ከሚስተር ሮዤ ሁዪዜንጋ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ ተመርኩዞ የተጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7548

No comments:

Post a Comment