Friday, September 27, 2013

ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙ መኪኖች ወደ ሰሜን ማቅናታቸው ተዘገበ


መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት 30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል።
መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment