የቀድሞዋ የመንግስት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ሃገር ቤት ከሚታተመው ሎሚ መጽሔት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳቸው ዘንድ ቃለ ምልልሱን እንደወረደ አስተናገድነው…
ሁሉ ነገር ራዕይ ሆኖ ይቀጥላል እንዲባል አልፈልግም
በሥልጣን የሚመጣ ክብር ደግሞ ከሥልጣን ጋር አብሮ ይቀራል
ሎሚ፡- አምባሣደር ዮዲት እምሩ በሕይወትሽ ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠሩብሽ ይሰማል፤ እንዴትና ለምን?
ወ/ሮ ሰሎሜ፡- እሳቸው ከፈጠሩብኝ መነሣሣትና መነሳሳት ይልቅ አባቴ እሳቸውን ምሣሌ በማድረግ ውስጤ የፈጠረው መነሣሣት ነው የሚበልጠው፡፡ ልጅ እያለሁ እሣቸው አምባሣደር ነበሩና በቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ይታዩ ነበር፡፡ የዛን ጊዜ እኔ አራተኛ ክፍል ነበርኩ፡፡ ሁልጊዜም በቴሌቪዥን ሲመጡ አባቴ ይጠራኝና “…በቃ አንቺ ስታድጊ እሣቸው ስራ የላቸውም” ይለኝ ነበር፡፡ የእሱ አባባል ስታድጊ ስራቸውን ትወስጅባቺዋለሽ ዓይነት ነበር፡፡ የመጀመሪያዋ ሴት እንደዚህ ታላቅ የሚባል ስራ ይዘው በቴሌቪዥን መጥተው ያየኋቸው እሳቸው ናቸው፡፡ እሣቸው ላይ ይበልጥ ትኩረት እንድሰጥና እንድነቃቃ ያደረገው ደግሞ አባቴ ነው፡፡
ሎሚ፡- ያኔ ልጅ እያለሽ አምባሣደር ዮዲት የፈጠሩብሽ አይነት ስሜት አሁን በሌሎች ትናንሽ ሴት ልጆች ላይ መፍጠር ችያለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ?
ወ/ሮ ሰሎሜ፡- እንደዚያ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁሌም የምለው ነገር ነው፤ ሁሉም ሰው እዚህች ምድር የመጣው ለምክንያት ነው በሚለው አምናለሁ፡፡ ምክንያት ደግሞ የሆነ ተፅእኖ የሚያሣድር ማለት ነው፡፡ ያ ተፅእኖ ደግሞ ጥሩ ነገር ለመስራትና ለማነሳሳት አርአያ ለመሆን ቢሆን ደስ ይለኛል፡፡ ወጣት ሴቶች እሷን አይቼ ነው ይህን የሆንኩት ቢሉ ደስ ይለኛል፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ ከአንዳንድ ሴቶች ጋር ስንገናኝ… “አንቺ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ቃል አቀባይ በነበርሽበት ወቅት የምትናገሪውን እሰማ ነበር፤… በዛ ምክንያት እንዲሕ አድርጌ…” ሲሉኝ ደስ ይለኛል፡፡ በርግጥ እነሱ ይህንን ይላሉ፣ ወደፊት እንዲሕ እባላለሁ… ብዬ ባልንቀሳቀስም… መንገዱ ግን ያንን ፈጥሮ ከሄደ በጣም ደስ ይላል፡፡ እናም እፈጥራለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሎሚ፡- የሕይወት ፍልስፍናሽ ምንድን ነው?
ወ/ሮ ሰሎሜ፡- ከባድ ጥያቄ ነው ብዙ ጊዜ የሚከብደኝ ጥያቄ የሕይወት ፍልስፍናሽ ምንድነው የሚለው ነው፡፡ በአንድ ወቅት የነበረ ፍልስፍና በሌላ ወቅት ሊቀየር አይችልም ወይ ብዬ አስባለሁ፡፡ በተለይ የራሴን ወደኋላ መለስ ብዬ ሳስታውስ… ከልጅነቴ ጀምሮ የያዝኩት ፍልስፍና ነው ለማለት ይከብደኛል፡፡ ምክንያቱም ፍልስፍናን ራሱን ለመተግበር አቅም ይጠይቃል፡፡ ግን አሁን ዛሬ በአጭሩ ምንድነው ፍልስፍናሽ ብትለኝ በዚህች ምድር ላይ ዱካ የጣለ፣ ኮቴ የነበረው ሰው፣ ኮቴው የተሰማ ሰው ሆኖ ማለፍ፡፡ …read more

Via: Zehabesha
No comments:
Post a Comment