Friday, September 6, 2013

Sport: ቀነኒሳ በሪዮ ዲ ጄኔሪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን ሊወዳደር ነው

በመጪው መስከረም ቀን 2006 .ም 
 ከአገሩ ልጅ ከኃይሌ ገብረሥላሴና ከእንግሊዛዊው ሞሐመድ ፋራህ ጋር ለሚያደርገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ቀነኒሳ በቀለ በአውሮፓውያኑ 2016 
በብራዚሏ ሪዮ ዲ ጄኔሪዮ በሚካሄደው ኦሊምፒክ ላይ አገሩን በማራቶን የመወከል እቅድ እንዳለው መግለጹን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።የትራክ (መም
ውድድሮች ኃያሉ ቀነኒሳ በቀለ ከአትሌቲክስ ስፖርት ስለመገለል የማሰቢያ ጊዜው ገና መሆኑንና ለረጅም ጊዜ አብሮት ከቆየው ጉዳቱ መላቀቁንና ወደ ብቃቱ መመለሱን በመስከረም ስድስቱ የግማሽ ማራቶን ውድድሩ ማሳየት እንደሚሻ ተናግሯል።
 የአምስትና አስር ሺ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለ በግማሽ ማራቶን ውድድር ታሪክ ምርጡ እንደሚሆን በአዘጋጆቹ በመነገር ላይ በሚገኘው የእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ ራን ውድድር ራሱን የሚያይበት እንደሚሆንም ገልጿል።
አትሌቱ « በአምስትና አስር ሺ ሜትር ውድድሮች ታላላቅ ክብሮችን አግኝቻለሁ። አሁን ትልቁ ግቤ በማራቶንና በግማሽ ማራቶንም ያንን ስኬት መድገም ነው። በርቀቶቹ የዓለም ክብረ ወሰንን እስከማሻሻል የሚደርስ ነው ፍላጎቴ። ከሁሉም በላይ ትልቁ ግቤ በሪዮ ዲ ጄኔሪዮ በማራቶን አገሬን በማራቶን መወከል ነው» ማለቱን ዘገባው አስነብቧል።

31 ዓመቱ ቀነኒሳ በአቴንስ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ባለቤት ሆኖ ከአራት ዓመት በኋላ በአውሮፓውያኑ 
2008 በቻይናዋ ቤጂንግ በተደረገው ኦሊምፒክ በአምስትና አስር ሺ ውድድሮች የድርብ ድል ባለቤት መሆን መቻሉ ይታወሳል።

ከቤጂንግ ኦሊምፒክ በኋላ በደረሰበት ጉዳት የቀድሞ ብቃቱን እንዳያሳይ ተጽዕኖ አሳድሮበት በለንደን ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር አራተኛ ሲወጣ በቅርቡ ከተጠናቀቀው የሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና ውጪ ሆኗል።

« በዓለም ውድድሮች ለመሳተፍና ወደ ትክክለኛው አቋሜና ብቃቴ ለመመለስ እየጣርኩ እገኛለሁ ። በእዚህ እድሜ ላይ ሆኜ ከስፖርቱ መገለል አልፈልግም። በመሆኑም በቅርቡ ወደ ቀድሞ ብቃቴ እመለሳለሁ ብዬ አስባለሁ» ብሏል። 
ቀነኒሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፍበት የግማሽ ማራቶን ውድድር ፈታኝና አዘጋጆቹ እንደገለጹት ምርጡ እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል።

ሱሉልታ አካባቢ ባስገነባው የመሮጫ መም ላይ ከወንድሙ ጋር ልምምዱን በመሥራት ላይ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ በእንግሊዙ የ
21 ነጥብ አንድ ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ የኃይሌ ገብረ ሥላሴ የዓመታት የጎዳና ውድድሮች ልምድና የሞ ፋራህ ፈጣን የአጨራረስ ብቃት ፈታኝ እንደሚሆንበት ተገምቷል። አትሌቱ ይህን የመጀመሪያው የሆነውን የግማሽ ማራቶን ፍልሚያ በድል ለማጠናቀቅ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ለዜና ወኪሉ ተናግሯል።


የወቅቱ የአምስትና የአስር ሺ ሜትር የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ በሁለት የግማሽ ማራቶን ውድድሮች ላይ ተካፍሎ ሁለቱንም በድል ማጠናቀቅ ችሏል።

የአገሩ ልጅ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በርቀቱ የካበተ ልምድ ባለቤት ነው። በርቀቱ በአውሮፓውያኑ ከ 1993 እስከ ከ1999 
ባሉት ዓመታት መካከል አራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ሆኗል። ከሦስት ዓመት በፊት በኒውካስል የተደረገውን ውድድርም አሸንፏል። በርቀቱ 
58 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ የሆነ የግሉ ምርጥ ሰዓትም ማስመዝገብ ችሏል።

የቀነኒሳ ተፎካካሪዎች በግማሽ ማራቶን ከእርሱ የተሻለ ልምድ ያላቸው በመሆኑ አትሌት ቀነኒሳ እነርሱን ለመቋቋም በማሰብ በሳምንት ለሰባት ቀን፣ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ በመሥራት ላይ ይገኛል።

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7116

No comments:

Post a Comment