Wednesday, September 4, 2013

ፖሊስ 4 የአንድነት አባላትን በአዳማ በማሰር የሚበትኑትን ወረቀት ነጠቀ

http://www.zehabesha.com/
አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለውን የሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ
በአዳማ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መጥራቱ የሚታወስ ሲሆን ለዚህ
ሰላማዊ ሰልፍ መሳካት ሕዝብ እንዲያውቅ ወረቀት በመበተን እየቀሰቀሱ
የሚገኙ የድርጅቱን አባላት ገዢው ፓርቲ ማዋከቡን ቀጥሏል። በዚህም
መሠረት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ
እንዳመለከተው በቅስቀሳ ስራ ላይ የነበሩ አራት የአንድነት ፓርቲ አባላት
አዳማ ከተማ ውስጥ ታስረዋል።
ፖሊስ ከ5ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን እንደቀማቸው የገለጸው የሚሊዮኖች
ድምጽ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እውቅና ተሰጣችሁ እንጂ በራሪ
ወረቀት የመበተን ፍቃድ የላችሁም በሚል
1ኛ. ዳንኤል ፈይሳ፣
2ኛ. ደረጄ መኮንን፣
3ኛ. አስናቀ ሸንገማ
4ኛ ደረጄ ክበበው የተባሉት አባላት ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው ከሰዓታት በኋላ መለቀቃቸውን
የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አስታውቀዋል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ፣ ከፖሊስ፣ ከደህንነት፣ከ ደንብ አስከባሪና ከሚሊሻ
የተውጣጡ ስምንት ግለሰቦች የአንድነት አባላትን በማሰሩ ተግባር እንደተሳተፉና የተወሰኑት ደህንነቶችና ፖሊስ
የድብደባ ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዳማ ከተማ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ስኬታማ የቅስቀሳ ስራ እያከናወነ
እንደሚገኝ የሚሊዮኖች ለነፃነት እንቅስቃሴ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment