Thursday, September 5, 2013

በአንድነት ፓርቲ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚታየው ምዝበራ አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር መገደላቸው የእለቱ ዋና ዋና የዜና ርእሶች ናቸው

በአዳማ/ ናዝሬት  የአንድነት ፓርቲ አባላት መዋከባቸው ታውቀ
ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ / ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በከተማዋ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ ወረቆቶችን ሲበትኑ የነበሩ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ተፈተዋል። ፓርቲው ሰለማዊ ሰልፍ እንዲአካሂደ ፈቃድ ከተሰጠው በሁዋላ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንጅ ወረቀት የመበተን ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ሰበብ ወጣቶቹ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል።
ኢሳት ከኢህአዴግ የአዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች ፓርቲው የሚያደርገውን ቅስቀሳ እንዲያስተጓጉሉ ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል። በኦሮሚያ ክልል ነፍጠኞች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙበት እድል ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት የኦህዴድ አመራሮች በመናገር ላይ ናቸው።
ከእነዚሁ ምንጮች ለመረዳት እንደሚቻለው የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ በግንባሩ ውስጥ ከሚታየው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ፣ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች አስጨንቋቸዋል። ከሁሉም የኢህአዴግ ድርጅቶች  በኦህዴድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ተስፋ መቁረጥ እንደሚታይ የሚገልጹት ምንጮች ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱንም ይገልጻሉ።
የአንድነት ፓርቲ በናዝሬት የሚያካሂደው ሰልፍ ለኦህዴድ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆናል በማለት እነዚሁ ምንጮች ተናግረዋል። በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናትም ወከባው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።


አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ለማካሄድ አቅዶት የነበረው ሰልፍ በኦህዴድ አመራሮች እንዲስተጓጎል መደረጉ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment