Wednesday, October 9, 2013

አኔ የሚወራዉን ነገር ልንገራችሁ..እናንት ደሞ የራሳችሁን ጨምሩበት፤( EthioTube Play)

"አቶ ተካ አስፋዉ በአፍሪካ ዋንጫዉ የቡድን መሪ ነበሩ፤ለተጫዋቾች ጥያቔ ፈጣን መልስ ለመስጠት ከማንም ቀድመዉም ይገኙ ነበር፤ተጫዋቾቹም ከማንም በፊት እኝህን ሰዉ መልስ እንደሚሰጥዋቸዉ እምነት አላቸዉ፤ከ2ት ሳምንት በፊት ሰዉየዉ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ቦታዉን እንደማይፈልጉት–ከፍተኛ ጫና እና ስድብ እንዳስተናገዱበት…ነገር ግን በሚያዩት ለዉጥ ደስተኛ እንደሆኑና ለፕሬዝንትነት ለመወዳደር እርግጠኛ እንዳልሆኑ ነገሩኝ!!
ትላንት እጩ መሆናቸዉ ተረጋገጠ፤ዛሬ ደሞ ትላንት ማምሻዉን በደረሰኝ የጽሁፍ መልእክትና ከዛ በሁዋላ ባወራሁት ስልክ ምክንያት በገዛ ፍቃዴ ከፕሬዝዳንትነት ዉድድር ወጥቻለሁ አሉ፤"

አኔ የሚወራዉን ነገር ልንገራችሁ..እናንት ደሞ የራሳችሁን ጨምሩበት፤
ነገሩ የተጀመረዉ የዣሬ 6ወር እንደሆነ ይነገራል፤የደቡቡ ክልል እጩ ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑም ይታወቃል፤9ኙ ስራ አስፈጻሚዎችም አንዲሁ…..ሀሳቡ የመነጨዉ ፌዴሬሽኑን ከወገንተኝት ለማንጻት በሚል እንደሆነ–ከአቶ ተካ የመጨረሻ ንግግርም መረዳት–ይቻላል፤እናም 5ት ሰዎች ይወዳደሩ እንጂ ምርጫዉ ቀድሞ ያለቀ ነዉ፤ክለቦችም ይሄ መረጃ ቀድመዉ እንዳላቸዉ..ክልሎችም በተመሳሳይ ለማን ድምጽ እንደሚሰጡ የታወቀ ነዉ፤እንደዉም ዛሬ ወይም ነገ በማለዳ ቀሪ በገዛ ፍቃዳቸዉ የሚለቁ ሰዎች እንደሚኖሩም ይታወቃል፤አንዳንድ የአዲስ አበባ ክለቦች ከተሰጣቸዉ ሀሳብ ዉጭ ሌላ ሰዉ ሊመርጡ እንደሚችሉ ፍንጭ ቢኖርም ባብዛኛዉ ግን ለደቡብ ክልል ተወካዩ እንደሚሰጡ ይጠበቃል
አቶ ተካ ዛሬ በጠቅላላ ጉባኤዉ ፊት ሀሳባቸዉን በንዴት ና ሀዘን ነበር የተናገሩት…ትላንት ምሽት ከስብሰባዉ መልስ አንድ በጣም ከሚቀርቡት ትልቅ ሰዉ የጽሁፍ መልእክት እንደደረሳቸዉና ከዛም በስልክ እንዳወሩት በስተመጨረሻም የመልቀቅ ዉሳኔ ላይ እንደደረሱ ገልጻዋል፤ዉስጥ ዉስጡን እየተሰሩ ነበር ያልዋቸዉ የሚያሳፍሩ ድርጊቶች አንዳንዱ ከጐጥም አንዳንዱ ከክለብ ዉግንናም ጋር የተያያዙ እነደነበሩ ፍንጭ ሰጥተዋል!!
ከዚህ ንግግር በኋላ የፕሬዝዳንትነት ጡዘቱ መሬት የነካ ይመስላል፤ምክንያቱም ሁሉም አፍ ላይ ያለዉ ቃል…የቀሩት 3ት ተወዳዳሪዎች መቼ ነዉ አቶ ተካን የሚከተሉት የሚል ነዉ!!በፎቶዉ ላይ የምትመለከትዋቸዉ የቀድሞ የፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ከንግዲህ ሩጫቸዉን ለጤና ብቻ ያደርጋሉ ማለት ነዉ!!የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የህግ አማካሪ….ከዛም የሜድሮክ ጉዳዮች ጠበቃ የነበሩት አቶ ተካ ከሁሉም የስራ አስፈጻሚ በተለየ ጨዋታ በስታድየም ተገኝቶ በመመልከት የኳስ ፍቅራቸዉን በተግባር ያሳዩ ሰዉ ነበሩ!!እሳቸዉን የሚተካዉስ?????ለማንኛዉም 4ቱ ጠርሞሶች መሀል ለመጨረሻዉ ዉድድር የሚቀርበዉ 1ዱ ብቻ እንደሆነ ከዋናዉ ምርጫ በፊት የተለየ ይመስላል!!3ቱ በቅደም ተከተል እንደሚወድቁ ይጠበቃል!!

No comments:

Post a Comment