Wednesday, October 2, 2013

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ ነዉ የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) .

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ መቷል:: የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል:: በከፍተኛ ደረጃ በሙስና በመዘፈቅ ያለአግባብ ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ለቁጥር የማይገመት ሃብት አፍርተዋል የተባሉት ሃያሁለት አከባቢ የሚገኘው የኮሜት ሕንጻ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብረስላሴ ሃይለማርያም (አለቃ ገብረስላሴ) በቀጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በባለስልጣናት ዙሪያ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል:: የካፒታል ሆተል ባለቤት የሆነው ልጃቸውም እንዲሁ ሁኔታዎቹ እየተጣሩ ሲሆን የአለቃ ገብረስላሴ የሙስና መዝገቦች ከገብረዋህድ ጋር የተቆራኙ እና ከዚህም ጋር በተያያዘ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ይውላሉ ተብሎ ይጠበቃል:: የሙስና ንሰሃ አባት የሚባሉት እና በአቋራጭ የከበሩት በማናለብጭነት እና በትዕቢት በመንግስት ባለስልጣናት የሚመኩት አለቃ ገብረስላሴ ባለፉት አራት ወራት ከተያዙት እና የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ከሚባሉት መላኩ ፋንታ;ገብረዋህድ ወ/ጊ;ነጋ ገ/እግዜር;ስማቸው ከበደ ከተማ ከበደ እና ሌሎች የሙስና ባላባቶች ጋር እንደተያዙ ወዲያውኑ የቃሊቲን ቂሊንጦ ጎራ ተቀላቅለዋል:: እስካሁን ድረስ በፍርድ ቤት የቀረበባቸው የክስ ዝርዝር ባይታወቅም በመጪው የጥቅምት 14 እና 18 2013 ክሱ የሚሰማ መሆኑ ታውቋል::ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት አለቃ ገብረስላሴ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቃሊቲ መውረዳቸው አጠያያቂ ነው ሲሉ ተደምጥጠዋል::ሆኖም እንደመርማሪዎቹ ምንጮች ከሆነ የተከሰሱት በገብረዋህድ መዝገብ ጋር በአንድነት እንደሆነ ታውቋል:: ፋይሉ አከባቢ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በተከለከለው ከፍራንኮ ቫሉታ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ሲሚንቶ አስገብተዋል የተለያዩ እቃዎችን ቀረጥ ሳይከፍሉ አስገብተዋል በጉቦ እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ወዘት የሙስና ተግባራት ከባለስልጣናት ጋር ተመሳጥረዋል በሚለው ፋይል የተካተቱ ሲሆን በዚህ ፋይል ደሞ የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ገብረዋህድ እና ሚስቱ ሃይማኖት እንዲሁም የሰየ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ ይገኙበታል:: — 

No comments:

Post a Comment