Wednesday, October 23, 2013

በነቀምት ሆስፒታል 10 እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በነቀምት ሆስፒታል በቅርቡ 10 እናቶች በወሊድ ምክንያት መሞታቸውን እና ፤ አንድ ሊትር ደም እስከ ሶስት ሺህ ብር መሸጡም ተጠቁሟል፡፡ በሆስፒታሉ ችግሩ እየከፋ በመሄዱ ወላድ እናቶች እና ታካሚዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ባለማግኘታቸው በዚሁ ሆስፒታል 10 እናቶች ህይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ጉዳዩን አውቆት በስብሰባ መድረክ ያነሳው ቢሆንም እስካሁን የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ የሆስፒታሉ ተገልጋዮች ቅሬታ እንዳደረባቸው ኢቲዮ ምህዳር ጋዜጣ በዛሬው ዘገባ አስታውቋል፡፡ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም እያለ መፈክር ቢያስነግርም በተግባር ግን የነፍሰጡር እናቶች ህልፈት እየተባባሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ጠቁማሉ፡፡

No comments:

Post a Comment