Monday, October 7, 2013

መንግስት በመንግስት መ/ቤት እና በት/ት ተቋማት ሰላት መስገድም ሆነ (ሂጃብ) መልበስ አክራሪነት በመሆኑ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች እና ባለ ድርሻ አካላት ሊዋጋው እንደሚገባ አስጠነቀቀ

Source: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
መንግስት በመንግስት /ቤት እና በት/ ተቋማት ሰላት መስገድም ሆነ ሀማኖታዊ ልብስ (ሂጃብ) መልበስ አክራሪነት በመሆኑን ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች እና ባለ ድርሻ አካላት ሊዋጋው እንደሚገባ አስጠነቀቀ፡፡#Ethiopia #EthioMuslims

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አመት እና አዲስ የስራ ዘመን ሲመጣ ዜጎችን በመልካም ተነሳሽነትና በብሩህ ተስፋ ወደ ልማትና ስራ ታጥቆ ከመዘጋጀትና ከመስራት ይልቅ ጠባብነት የተጠናወተዉ ጭፍን የፖቲካ ጥላቻን ለመላዉ ህዝብ የተለየ መድረክ እያዘጋጀ ፀረ ህዝብ የሆነ ፕሮፖጋንዳዎችን እያስተላለፈ እንደሚገኝ ምንጮች አስታወቁ፡፡

በዘንድሮም አመት ከባለፉት አመታት በባሰ ሁናቴ የዜጎችን በህገመንግስቱ የተጎናፀፉትን የእምነት ነፃነት መብት መጣስ ብቻ ሳይሆን ከነአካቴዉ ለማጥፋት እየሰራ እንዴሆነ የሚያሳዩ ተግባራቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከነዚህም ተግባራት መካከል አሁን ባለንበተ የመስከረም ወር ውስጥ በበርካታ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና (ዩኒቨርሲቲዎች) ፣የመንግስት /ቤቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች የመንግስትን አክራሪ አቋም እየሰበኩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢተዮ ቴሌኮም የተካሄዱትን ስብሰባዎች አይነተኛ ማሳያ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን መምህራኖች በፊት አዉራሪነት ሰብስበዉ የነበሩት የፌደራል ጉዳይ ሚንስቴር ባለስልጣናት ሲሆኑ ከነዚህም መካከል አቶ ፋንታ፣ አቶ ታየ፣ አቶ ዳምጠዉ እና / ሽፈራዉ እንደነበሩ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በተለይ አቶ ታዬ በሰፊዉ የመንግስትን የአክራሪነት ፕሮፓጋንዳ በስብሰባው ላይ ሲያብራሩ የቆዩ ሲሆን በንግግራቸውም መሃልም በርካታ ፀረ ህገ መንግስት የሆኑ ንግግሮችን ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡ከነዚህም መካከልሀማኖታዊ ልብስ (ሂጃብ) መልበስ የሚከለክል መመሪያ አዉጡ፡፡ ይህንን መመሪያ የሚተላላፍ ካለ ልክ እንደባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እርምጃ ዉሰዱበትሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከተሰብሳቢዎቹ መምህራን መካከል / ቢንያም የተባሉ ምሁር ከመድረኩ በኩል ሲነዛ የነበረውን ፕሮፓጋንዳ አድምጠው ከጨረሱ ቡሃላ በመድረክ ላይ የነበሩትን ባለስልጣናትን አቀራረባቸዉም ይሁን ያቀረቡት ፅሁፍ ተሰብሳቢዉን የማይመጥን ተራ የፖለቲካ ሰባካ ነዉ ብለዉ ካጣጣሉት በኋላ በቀረበዉ ፅሁፍ መሰረት መንግስት እራሱ አክራሪ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉን ምንጫችን ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ይህ ምሁር የትምህርት ተቋሞች እየተመሩ ያሉት በምሁር ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝ በሆነ ሰዉ ነዉ ብለዋል፡፡ በመንግስት አመለካከት የትምህርት ጥራት የሚለካዉ በፖለቲካ ታማኝነት እንደሆነም አስረግጠዉ ነግረዋቸዋል፡፡ በተጨማሪም መንግስት በየቤተክርስቲያኑና በየመስጂዱ እየገባ አንተ አሰግድ አንተ ምራ ማለቱ ከጣልቃ ገብተነት በላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም በኢተዮ ቴሌኮም የኮምኒኬሽን ሚንስትር የሆኑት / ደብረፂዎን የቴሌን ሰራተኖች ሰብስበዉ እኛ በሴኩላሪዝም ስለሆነ የምንመራዉ በሴኩላር ተቋም ዉስት ማንም ሰዉ መስገድ አይችልም፡፡ የሀይማኖት ተግባር የሚፈፅም ካለ አክራሪ ነዉ ማለታቸዉን ምንጮች ዘግበዋል፡፡ አያይዞም በተለየ ሁኔታ / ደብረፂዎን ሀይማኖትን ማጥላላትና ፍፁም አምባገነንነት በተሞላበት መልኩ የፈለገ እቤቱ ሲመለስ ሰብስቦ ይስገድ ሲሉ መንግስታዊ ፈትዋ ቢጤ መስጠታቸውንም ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በዘንድሮ አመት በመንግስት በተያዘው እቅድ መሰረት በየመስሪያ ቤቱ ሙስሊም በመሆናቸው የሰላት ወቅት ሲደርስ ሰላት የሚሰግዱ፣ ሙስሊም በመሆናቸው ሂጃባቸውን የሚጠብቁ ሴት እህቶቻችን በአክራሪነት በመፈረጃቸው ስራቸውን ወይም ደግሞ አክራሪነታቸውን እንዲመርጡ በማድረግ ከስራ ገበታቸው የማፈናቀል ዘመቻ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

በተመሳሰይም በምህር ተቋማት ውስጥም ሰላት የሚሰግድ እና ሂጃቧን የምትጠብቅ ሴት ተማሪ አክራሪ በመሆኗ ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተዘግቧል፡

No comments:

Post a Comment