በአፍቃሬ ወያኔነቷ የምትታወቀዉና ወያኔን ተከትላ ከዋሺንግተን ዲሲ አዲስ አበባ የገባቸዉ የምላስ እመቤቷ ሚሚ ስብሀቱ የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ወይንም ፕሬስ ካውንስል ታቋቁማለች ተብሎ የተጣለባትን ወያኔያዊ አደራ መወጣት እንዳቃታት ታወቀ። ከወያኔ ጋር ባላቸዉ ንክኪ የተነሳ በገዢዉ ፓርቲ ደጋፊነታቸዉ በሚታወቁት በሚሚ ስብሃቱ ሊ/
መንበርነትና በአማረ አረጋዊ ምክትል ሊ/መንበርነት የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስ በርስ ባለመግባባቱና የብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ የዉኃ ሽታ ሆኖ እንደቀረ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በሚሚ ስብሀቱና በአማረ አረጋዊ መሪነት ስራዉን የጀመረዉ ኮሚቴ ሶስት አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም በሁለቱ ዝናና ስም ናፋቂ ሰዎች መካከል በተፈጠረዉ ግልጽ የስልጣን ሽኩቻና መናናቅ ምክንያት ምስረታውን ማካሄድ እንዳልተቻለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል። አሁን በስራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙሃን ህግ በሚረቀቅበት ወቅት መንግስት የፕሬስ ካውንስል እንደሚያቋቁም ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም በተለይ በግሉ ፕሬስ ያልተቆጠበ ተቃውሞ ረቂቅ ህጉ ተሻሽሎ እንዲወጣና በተሻሻለውም ሕግ መሰረት ፕሬስ ካውንስሉን የማቋቋሙ ኃላፊነት የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል።
የፕሬስ ካውንስሉ ቢቋቋም በተለይ ጋዜጠኞች በትንሽ በትልቁ ጉዳይ ፍ/ቤትና ፖሊስ ጣቢያዎች የሚመላለሱበትን በማስቀረት የሚቀርቡ ክሶችና ቅሬታዎች በአስተዳደራዊ መንገድ መፍትሔ ለማስገኘት ይረዳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር።
ከምርጫ 1997 በፊት 385 በላይ ጋዜጦችና መጽሔቶች የነበሩት በአሁኑ ወቅት እጅግ አሽቆልቁለው (8.5 %) 16 ጋዜጦችና 17 መጽሔቶች ብቻ በህትመት ላይ ይገኛሉ። በአንጻሩ በመንግስት የተያዙ የራዲዮና የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ቁጥር አድጎ በጠቅላላው 23 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 15 ያህሉ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች፣ ራዲዮ ፋናን ጨምሮ 5 የግል ራዲዮ ጣቢያዎች፣ 10 የመንግስት ጣቢያዎች 1 የቴሌቪዝንና፣ 3 የክልል ጣቢዎች ይገኙበታል።
By: mesfin
No comments:
Post a Comment