Thursday, October 24, 2013

በራያ ቆቦ በመኪና አደጋ 26 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ  ጥቅምት 14 2006 (ኤፍ  በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ትናንት በደረሰ የመኪና አደጋ የ31 ሰዎች ህይወት ወዲያው  ሲያልፍ በቀሪዎቹ ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።
አደጋው የደረሰበት አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ የመጫን አቅሙ 24 ሰው ሲሆን ነገር ግን 43 ሰዎች ጭኖ ከቆቦ ወደ ዞብላ ሲጓዝ ነበር።
ከቆቦ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከርቦ በምትባለው አካባቢ ሲደርስ 200 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ውስጥ በመግባተቱ ነው አደጋው የደረሰው።
የጉዳቱ መጠን ከፍ ያለ በመሆኑም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችለ ተገልጿል።
አሽከርካሪና ረዳቱ  በወቅቱ ያመለጡ ቢሆንም ፥  በአሁኑ ወቅት ግን አሽከርካሪው  በቁጥጥር ስር መዋሉ  ተመልክቷል።

በሁሴን ግዛው
via fanabc.com

No comments:

Post a Comment