Wednesday, October 23, 2013

ስብሃት ነጋ በመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ተገለጸ

(ዘ-ሐበሻ) አዛውንቱ የሕወሐት መስራች ስብሃት ነጋ በመርሳት በሽታ (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ለአዛውንቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገለጹ። ምንጮች በተለያዩ ሁኔታዎች እንደገለጹት ስብሃት በየመድረኩ አንድ ጊዜ የተናገሩትን በሌላኛው ጊዜ የማይደግሙት፣ ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ ከተለያዩ የኢሕአዴግ ሰዎች ጋር የሚላተሙት ወይም ጥያቄ ሲጠየቁ አላስታውስም የሚሉት የዳመንሺያ ተጠቂ በመሆናቸው መሆኑን የህክምና ባለሙያዎችን ጥናት ያሰባሰቡት እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል። 


ስማቸው እንዳይገለጽ የሚፈልጉት እነዚሁ ምንጮች አቶ መለስ በሞቱበት ወቅት 33 ጀነራሎች ከተሾሙ በኋላ መሾማቸውን በሰሞኑ ቃለምልልሳቸው ላይ አላውቅም/አላስታውስም/ ማለታቸውንና ሌሎችንም በመጥቀስ፤ እነዚሁ ምንጮች ከህክምና ባለሙያዎች እንዳገኙት ጥቆማ “የመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) ምንድን ነው?” የሚለውን ሲያብራሩ፦
“ከባድ  የመርሳት    ችግር  ይህ   ነው   የሚባል   በሽታ     አይደለም።   ይልቁንም     አእምሮን  በሚያውኩ የተለያዩ እክሎች   ምክንያት     የሚፈጠሩ   የህመም   ምልክቶች አጠቃላይ  መገለጫ     ነው፡፡  የከባድ    የመርሳት  ችግር ተጠቂዎች    አእምሯዊ    አተገባበራቸው  እጅጉን    በመስተጓጎሉ  የእለት     ተለት     ተግባራቸውና    ከሰዎች ጋር    ያላቸውን    ግንኙነት  ይጎዳል፡፡    እንዲሁም ግልፍተኝነት፣   የቀን   ቅዠት እና     በሌለ  ነገር    ማመን የመሳሰሉት   ሁኔታዎች     ስለሚያጋጥሟቸው  ለከባድ    ባህሪያዊ   ችግሮች   ሊዳረጉና     ማንነታቸውን   ሊያጡ  ይችላሉ።  የማስታወስ   ችሎታ    መቀነስ     የዚህ   ህመም    የተለመደ  ምልክት ቢሆንም የማስታወስ ችሎታው የቀነሰ ሰው በሙሉ የከባድ የመርሳት ችግር ተጠቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡” ይላሉ።
እነዚህ ችግሮች በስብሃት ላይ በየጊዜው እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ምንጮች ”በሽታውን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲያብራሩም “ለከባድ የመርሳት ችግር የመጋለጥ እድልን ከፍ ሊያደርጉ  ከሚችሉ ሁኔታዎች ውስጥ ቀጥሎ የተጠቀሱት ይገኙበታል፡-

• ከዘር የመጣ ከሆነ
• በአንጎል ውስጥ የሚከሰቱ እክሎች ካሉ
• የደም ዝውውርንና ወደ አንጎል የሚያመራውን ጤነኛ የደም ዝውውርን የሚያውክ በሽታ ከተከሰተ
• የኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ መኖር (በተለይ ኤችአይቪ በደሙ ያለበት ሰው የኤድስ ታማሚነት ደረጃ ከደረሰ)” በማለት ይጠቅሳሉ።
የህክምና ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የሚገልጹት እነዚሁ ምንጮች “የከባድ መርሳት ችግር ምልክቶች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲገልጹም “አብዛኛውን ጊዜ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ከባድ የመርሳት ችግር ቀዳሚና በጉልህ የሚታይ ምልክት ነው፡፡
የሚከተሉትም ሌሎች ምልክቶች ናቸው፡-
• የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ማስታወስ ማዳገት • በደንብ የሚያውቋቸውን ሰዎችና ቦታዎች መዘንጋት
• ሀሳብን ለመግለጽና ቁሶችን በስማቸው ለመጥራት ትክክለኛ ቃላትን ለማግኘት በእጅጉ መቸገር
• የሂሳብ ስሌቶችን መስራት ማዳገት
• እቅድ ለማውጣትና ስራን ለመፈጸም መቸገር
• ለመወሰን መቸገር፥ ለምሳሌ በአጣዳፊና አደገኛ ሁኔታ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባ አለማወቅ
• የራስን ባህሪይና ስሜት ለመቆጣጠር መቸገር፤ለምሳሌ ግልፍተኛ ወይም ቁጡ መሆን
• አዘውትሮ መደበት
• ራስን አለመንከባከብ፤ ለምሳሌ የግል ንጽህንናን አለመጠበቅ” ናቸው ይላሉ።
“በአንድ ሰው ላይ ቀደም ሲል የተገለጹት ምልክቶች የሚታዩና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ የሚንጸባረቁ ከሆነ ያለምንም ማመንታት በቶሎ ወደ ሆስፒታሎችና የጤና ማእከላት መሄድና የባለሙያ የህክምና አገልግሎትና እንክብካቤ ማግኘት ይኖርበታል፡፡” ሲሉ የባለሙያዎችን ምክር የሚጠቅሱት እነዚሁ ምንጮች  በሽታውን እንዴት ማስታመም ይቻላል? የሚለውን ሲገልጹ ደግሞ
“የታዘዘላቸውን ህክምናና የሀኪም ምክር በአግባቡ እንዲከታተሉ ማገዝ፦
ከባድ የመርሳት ችግር ካልታከመ ወደከፋ ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ሆኖም ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች የሀኪምን ምክር በመከታተልና የታዘዘላቸውን ህክምና በአግባቡ በመከታተል ጤናማ ህይወት መምራት ይችላሉ። ለዚህም የጓደኛና የቤተሰብ ድጋፍ ወሳኝ ነው።
• ከባድ የመርሳት ችግር ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረግ፦
- ከባድ የመርሳት ችግር ያለባቸው ሰዎች ራሳችውን ወይም ሌሎችን ለጉዳት እንዳይዳርጉ
- ለመከላከል ከቤተሰብና ከጓደኞች ቋሚ እንክብካቤና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ለዕለት ተዕለት ተግባሮች ለምሳሌ ሲመገቡ፣ ሲታጠቡም ሆነ ሲለብሱ እርዳታ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
- በመኖሪያ አካባቢ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ማሸሽ፦
- አደጋ ሊያስከትሉባቸው የሚችሉ ነገሮችን ከፊታቸው ዞር ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ለምሳሌ እንደስለት ፣ አደገኛ ኬሚካሎች፣ ሹል ነገሮችንና መሳሪያዎችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
• ሊረብሹ የሚችሉ ሁኔታዎችን መቀነስ፦
በአንዳንድ ድርጊቶች ወይም በሚረብሹ ድምጾች ምክንያት ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ሊፈሩና ግራ ሊጋቡ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም አላስፈላጊ ድርጊቶችን ማስቆም፣ ሊጠይቁ የሚመጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ ቴሌቪዥንና ሌሎች የሚረብሹ ድምጾችን መቀነስ አስፈላጊ ነው፡፡
• ከባድ የመርሳት ችግር ያለባቸው ሰዎች እንዲዝናኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፦
የተለመዱ የመዝናኛ ተግባራቶቻቸውን መፈጸም   እንዲቀጥሉ ሊበረታቱ ይገባል፡፡ ለምሳሌ፤ የእጅ ስራዎች፣ ጨዋታ፣ ሙዚቃ የመሳሰሉት አዕምሮን ለማነቃቃትና ስሜታቸውን ሊያሻሽሉ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡” ይላሉ።
እነዚሁ የቅርብ ሰዎች ምናልባት አቶ ስብሃት ይህን ችግር እንዳለባቸው በሃኪም አልተነገራቸው ከሆነ በአስቸኳይ ህክምናውን እንዲከታተሉ ይመክራሉ።

No comments:

Post a Comment