Friday, October 18, 2013

የኑዛዜው መጨረሻ በአሜሪካ (ከኢየሩሳሌም አረአያ)

( ሰይፉ ይህ ነበር)
የኑዛዜው መጨረሻሰይፉ ይባላል፤ ለ25 አመት ገደማ በአሜሪካ ኖሯል። በዲሲ ከተማ በታክሲ ስራ ይተዳደር የነበረው ሰይፉ ከብቸኝነት ኑሮ ለመውጣት ሲል ከአመታት በፊት አዲስ አበባ ይሄድና ኒካ (ቀለበት) ያስራል። ወደ አሜሪካ ከተመለሰ በኋላ እጮኛውን ባሰበው ግዜ አላመጣትም። …የሚያፈቅራት እጮኛውን ያላመጣበት ምክንያት አሳዛኝ በመሆኑ ማለፍን መረጥኩ።…የካንሰር ህመምተኛ የሆነው ሰይፉ ከሶስት ሳምንት በፊት በጣም በመታመሙ ሆስፒታል ይገባል። ያለው እድሜ በቀናት ብቻ የሚቆጠሩ እንደሆኑ ዶክተሮች ይነግሩታል። ዘመድ አዝማድ የሌለው ሰይፉ በመጨረሻ እንዲህ ሲል ተናዘዘ፤ « ከሞትኩ በኋላ ሬሳዬን አቃጥሉት» ብሎ ተናገረ። ..የዚህ ወገን የህይወት ሩጫ መንገድ ቀረ። በዲሲ አንድ ሆቴል ጀርባ የሰይፉ ታክሲ ተገትራ ቆማለች። ሰይፉን በቅርብ የሚያውቀው ወዳጁ ታክሲዋን እያመለከተኝ ታሪኩን ከነገረኝ በኋላ፥ « ኑዛዜው ተፈፃሚ ሆነ..» ሲለኝ፣ ሃዘንና ድንጋጤ ስለወረረኝ ላስጨርሰው አልቻልኩም።..ግን ለምን?..ምን ምክንያት ቢኖረው ይሆን?...መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች በውስጤ ተመላለሱ።.. ድንገት ሌላም አሳዛኝ ነገር ታወሰኝ፤ በኩላሊት በሽታ ሲሰቃይ፣ ወገን ያልደረሰለት ታዋቂና አንጋፋ አርቲስት « ከሞትኩ በኋላ ማንም እንዲያለቅስልኝና እንዲቀብረኝ አልፈልግም። ..» ሲል በአሳዛኝ ሁኔታ የገዛ ራሱን በእሳት አቃጥሎ ማለፉን በዲሲ ከሚገኙ የሃበሻ ራዲዮ የሰማሁት ታወሰኝ። ..ነፍስ ይማር!! አወይ ወገኖቼ!..   ( ሰይፉ ይህ ነበር)ሰይፉ ይባላል፤ ለ25 አመት ገደማ በአሜሪካ ኖሯል። በዲሲ ከተማ በታክሲ ስራ ይተዳደር የነበረው ሰይፉ ከብቸኝነት ኑሮ ለመውጣት ሲል ከአመታት በፊት አዲስ አበባ ይሄድና ኒካ (ቀለበት) ያስራል። ወደ አሜሪካ ከተመለሰ በኋላ እጮኛውን ባሰበው ግዜ አላመጣትም። …የሚያፈቅራት እጮኛውን ያላመጣበት ምክንያት አሳዛኝ በመሆኑ ማለፍን መረጥኩ።…የካንሰር ህመምተኛ የሆነው ሰይፉ ከሶስት ሳምንት በፊት በጣም በመታመሙ ሆስፒታል ይገባል። ያለው እድሜ በቀናት ብቻ የሚቆጠሩ እንደሆኑ ዶክተሮች ይነግሩታል። ዘመድ አዝማድ የሌለው ሰይፉ በመጨረሻ እንዲህ ሲል ተናዘዘ፤ « ከሞትኩ በኋላ ሬሳዬን አቃጥሉት» ብሎ ተናገረ። ..የዚህ ወገን የህይወት ሩጫ መንገድ ቀረ። በዲሲ አንድ ሆቴል ጀርባ የሰይፉ ታክሲ ተገትራ ቆማለች። ሰይፉን በቅርብ የሚያውቀው ወዳጁ ታክሲዋን እያመለከተኝ ታሪኩን ከነገረኝ በኋላ፥ « ኑዛዜው ተፈፃሚ ሆነ..» ሲለኝ፣ ሃዘንና ድንጋጤ ስለወረረኝ ላስጨርሰው አልቻልኩም።..ግን ለምን?..ምን ምክንያት ቢኖረው ይሆን?…መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች በውስጤ ተመላለሱ።.. ድንገት ሌላም አሳዛኝ ነገር ታወሰኝ፤ በኩላሊት በሽታ ሲሰቃይ፣ ወገን ያልደረሰለት ታዋቂና አንጋፋ አርቲስት « ከሞትኩ በኋላ ማንም እንዲያለቅስልኝና እንዲቀብረኝ አልፈልግም። ..» ሲል በአሳዛኝ ሁኔታ የገዛ ራሱን በእሳት አቃጥሎ ማለፉን በዲሲ ከሚገኙ የሃበሻ ራዲዮ የሰማሁት ታወሰኝ። ..ነፍስ ይማር!! አወይ ወገኖቼ!..

Via: freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment