አሚን አስካር ያልተጫወተበት ቦታ በረኛ ብቻ ነዉ፤አሁን በኖርዌይ ሁለተኛዉ ትልቅ ቡድን የሚጫወተዉ በአመካይ አጥቂ ቦታ ነዉ፤”እኔ ለትዉልድ ሀገሬ ቡድን መጥቀም እፈልጋልሁ..በአለም ዋንጫ አልፌም መጫወት ለኢትዮጲያ ማገልገል እፈልጋልሁ”ብሎ ለሱፐር ስፖርት ተናግርዋል፤አስካር ለኖርዌይ ወጣት ቡድን ተመርጦ ተጫዉትዋል፤ለዋናዉ ብሂራዊ ቡድን ግን ለመጫወት አልፈለገም፤አሁን ለዋልያዉ ልጫወት ያለበት ወቅት ምናልባት ለአለም ዋንጫ ካለፋ እዛም ላይ የመካፈል ጉጉት አድሮበት እንደሆነም ያሳብቃል፤
የሰሞኑ ወሬ አስካር ወደ ዋልያዉ ይመጣል ወይ የሚል ነበር፤አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ተጫዋቹን ለናይጄሪያ ጨዋታ እንደማይፈልጉት ተናግረዋል፤እንደዉም ያልዋቸዉ ተጫዋቾች በቂ እንደሆኑ ጭምር አሳዉቀዋል፤
እዛዉ ኖርዌይ ለ2ተኛ ዲቪዝዮን ክለብ የሚጫወተዉ ኢትዮጵያዊ ሳሙኤል ወርቅነህ ግን ከሰዉነት የተለየ አስተያየት አለዉ፤ሳሙኤል ወደ ኖርዌይ ከመሄዱ በፊት እዚህ ሀገር ቤት ለደደቢት ተጫዉትዋል፤የኳስ ሜዳ ሰፈር ልጅም ነዉ፤አማካይ ስፍራ ላይ ይጫወታል፤እናም አስካር ለዋልያዉ ይጠቅም ነበር ባይ ሁንዋል፤
“በጣም ይመጥናል..አንደኛ ሰዉነት የሚፈልጋቸዉ ብቃቶች አሉት..ፍጥነት አለዉ..ጉልበተኛ ነዉ!!በዛ ላይ ሹተር ነዉ!!በዛ ላይ በኛ ቲም ከመሀል ተነስቶ በራሱ ጊዜ አንድ ነገር የሚፈጥር ተጫዋች የለዉም..ልጁ ክሬኤቲቭ አይደለም ነገር ግን በራሱ ተነስቶ የሆነ ነገር መፍጠር እና ማግባት ይችላል.በጣም ታጋይም ነዉ.እንደዉም ለናይጄሪያ ጨዋታ ብታስጠሩት አሪፍ ነዉ!!፤”
ብሎኛል ሳሙኤል…!!!አስካር በኖርዌይ ሊግ የአመቱን ድንቅ ግብ ሽልማትን ባለፈዉ የዉድድር ዘመን አሸንፍዋል፤በዋልያዉ ከአፍሪካ ዋንጫ በፊት ከዉጭ ትዉልደ ኢትዮጲያዎያንን አስመጥቶ አጫዉትዋል፤ፉአድና ዩሱፍ ይጠቀሳሉ፤ከዛ ወዲህ ዳዊት በሻህ ከጀርመን ለሙከራ መጥቶ ተቀንስዋል፤አሁን ለቡና ፈርሞ እየተጫወተ ይገኛል!!
ከኖርዌይ አስተያየቱን የሠጠኝ ሳሙኤል እሱም አንደኛ ዲቪዝዮን ሲጫወት ልመረጥ እንደሚል ፍንጭ ሰጥቶኛል፤”ዋልያዉን የምጠቅመዉ እኔ ነኝ” በሚልም ፍላጎቱን በቀልድ መልክ አስቀምጠዋል!!ወደ ፌስ ቡክ ገፁ ስታመሩ ደግሞ..የኛ ሰፈር ደመራ ወደ ብራዚል ወደቅ ነገር አለ..የሚል ሁፍ ታገኛላችሁ!!!ይቅናህ ብለናል ልጅ ሳሙኤል!!
No comments:
Post a Comment