Thursday, October 17, 2013

ባለፈዉ የኢትዮጽያና የናይጄርያ ጨዋታለት አንድ መለስ ዜናዊን ና ሰላዲን ሰኢድን ለይቶ የማያዉቅ ፌደራል ፖሊስ አጋጥሞኝ ነበረ::


ነገሩ ከዚህ ይጀምራል
እኔ እና ሌሎች ጎደኛቼ እስቴድየም
ለመግባት ሠልፍ ላይ ነበርን እናም
አንድ ልጅ ባጠገባችን እንዲ ሲል አለፈ 
የሰላዲንን ጉርድ ፎቶ
አንድ አንድ ብር
የጀግናዉን ጉርድ ፎቶ
አንድ አንድ ብር
አንድ አንድ ብር

እንዲ ሲል የሰማዉ የፌደራል ፖሊስም ልጁን ና አተ? አለዉ

ልጁም*--- መጣ እስቲ ፎቶዉን? አለዉ ልጁም*--- ሰጠዉ

ከዛ ፎቶዉን አየት አረገና ለምንድ ነዉ ጀግና አይሞትም ተብሎ ያለተፃፈበት ?
ልጁ*--- በመገረም ለምን እንደዛ ተብሎ ይፃፍበታል ኢሄ እኮ መለስ ዜናዊ አይደለም::
ታድያ ኢሄ ማነዉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋናዉና ምርጡ ተጫዋች ሰላዲን ሰኢድ ነዉ::
ፌደራሉም*--- እና ኢሔ ምኑ ጀግና ነዉ ጀግና አታዉቅም እንዴ ሂድ ከዚ ተንቀሳቀስ በቃ ብሎ ልጁን ገፍተር አደረገዉ::

ልጁም*--- በመልሱ በመበሳጨት እንዴት ነዉ አስተሳሰብህ? እንዴት ሰላዲንን ጀግና አይደለም ትለኛለህ? ሲለዉ ::

ፌደራሉ እኔን ነዉ እንዴት ነዉ አስተሳሰብህ ያልከኝ አለና አስተሳሰቡን ለማሳየት ነዉ መሠለኝ በያዘዉ ዱላ ማጅራቱን

ልጁም ወደቀ በወደቀበት ሊደግመዉ ሲል ባቅራብያዉ የነበሩ ልጆች መሀል ገብተዉ እባክህ ተወዉ ተሳስቶ ነዉ እንደዛ ያለህ ይቅርታ አርግለት ብለዉ ባያረጋጉት ኖሮ ያ ፋራ ፌደራል ፖሊስ በዛ ከ አመት ባል በላይ በነበረ ቀን ጉድ አድርጎት ነበር ::

"ከእንደዚ አይነት ፌደራል ፖሊስ ያርቃቹ"

//ፍቄ ቡርሼ// source:-//ፍቄ ቡርሼ//

1 comment:

  1. THESE ARE OUR guardians
    These are our police men
    Treating wild grabbing fame
    These are FEDERAL POLICE
    Showing the blunt of the gov’t

    These are our police men
    Loyal like a dog to the Tigrean
    These are our guardians
    Killing many innocents in dozens

    These are our policemen
    Pacifying democracy flame
    Through a thick log and anarchism
    Building the DAM of ethnicism

    (By Minasie Gessesse

    ReplyDelete