ከርዕሶም ኃይለ

ዘ-ሐበሻ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ናት።
በሌላም በኩል “ዶ/ር” ሙላቱ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ መጋቢት 1996ዓ.ም ፓርቲው ባደረገው ግምገማ በአቶ መለስ ከተዘለፉት አንዱ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን በመንተራስ «ኢትኦጵ» ጋዜጣ «ከሕወሐት መንደር ከቃረምኩት» በሚል አምዱ በወቅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንደዘገበው፥ « አቶ መለስ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ “ ሙላቱ – አንተን ሚ/ር አድርጌ መሾሜን ረስቸዋለሁ። ያለስራ በሚ/ርነት የተጎለትክ ነህ፤ እዛው ጃፓን አምባሳደር እንደሆንክ ብትቀር ይሻላል። ..ኦ.ህ.ዴ.ድ ማለት ለትግል ፈጥረነው የት እንደገባ የማይታወቅ ድርጅት ነው።” » በማለት መለስ ዜናዊ መናገራቸውን አመልክቶ ነበር።
የ“ዶ/ር” ሙላቱ ባለቤት ወ/ሮ መአዛ አብርሃም ትባላለች። ሸንቃጣዋና የደስ ደስ ያላት መአዛ አንድ ጃፓናዊ አግብታና ልጅ ወልዳ በቶኪዮ ከተማ ትኖር ነበር። እራሷን በጣም ስለምትጠብቅና አለባበሷን (አጭር ሚኒ ቁምጣ ነው የምትለብሰው) ለተመለከታት በወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነች አድርጎ ይገምታታል፤ ሃቁ ግን ወ/ሮ መአዛ 53 አመት እድሜ ይሆናታል። ከሙላቱ ተሾመ ጋር የተዋወቁት ጃፓን ነበር። መአዛ በጣም ብልጥ ሴት ናት። በጃፓን የኢትዮጲያ አምባሳደር የነበሩት ሙላቱ ተሾመን ታጠምዳለች። ያጠመደችው ወላጅ አባቷ አቶ አብርሃም ነጋ በቀይ ሽብር ወንጀል ተከሰው ስለታሰሩ ነበር። ጃፓናዊ የልጇን አባት ባሏን በመግፋት አምባሰድሩን ትቀርባለች። እንዳጋጣሚ አቶ ተሾመ የስራ ጊዚያቸውን ጨርሰው አገር ቤት ሲመጡ አብራ ትመጣለች። ክዛም ወላጅ አባቷን እንዲያስፈታላት ትጠይቃለች። የተጠየቁት ሙላቱ « ይህን በጭራሽ አልችልም። እነመለስ ከሰሙ ከእንጀራዬ ወዲያው ያባርሩኛል። ይህን ጥያቄ ዳግም እንዳትጠይቂኝ።» ይላሉ። ወላጅ አባቷ በ2000ዓ.ም ከእስር ተፈቱ። ወ/ሮ መአዛ ጃፓናዊ ባሏንና ልጇን በመተው ለፈፀመችው የትዳር ማፍረስ ተግባር ወደዛች አገር ዳግም እንዳትገባ ውሳኔ ስለተላለፈባት፣ ከ”ዶ/ር” ሙላቱ ጋር መጠቃለልን መረጠች። መአዛና ሙላቱ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ሙላቱ ተሾመ በ1994ዓ.ም በሰባት ሚሊዮን ብር በቦሌ ያስገነቡት ዘመናዊ ቪላ በወር 36ሺህ ብር እንደሚከራይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ ቪላውን ለመገንባት ገንዘቡ በሙስና እንዲገኝ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ባለቤታቸው ወ/ሮ መአዛ መሆናቸው ታውቋል።
No comments:
Post a Comment