Wednesday, October 9, 2013

ለዋልያዉ ሊፀለይ ነዉ

"ቦታዉ እዚህ እኛ ሰፈር ቄራ አከባቢ ነዉ፤የጎፋ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ዉስጥ ነዉ ነገርየዉ የታቀደዉ፤ርእሱ ዋልያዉን ለናይጄሪያ ጨዋታ በዝማሬና ጸሎት ማጀብ—እንዲያሸንፍ መጸለይ ነዉ፤የናይጄሪያ ሴኔት ፕሬዝዳንት አረንጓዴዉን ንስር በአለም ዋንጫ እንዲቀናዉ የ9ኝ ቀናት የጸሎት ፕሮግራም ማወጃቸዉ ይታወሳል፤አሁን ለዛ ምላሽ ነዉ ወይ የሚል ጥያቄ ያጭራል…ነገር ግን አስተባባሪዉና የሀሳቡ አመንጪ አክሊሉ ግን ስላልተሳካልኝ ነዉ እንጂ ይህንን ነገር ያሰብኩት ቀድሜ ነዉ ይላል፤"
በስልክ አናገርኩት!!
—ኳስ ታያለህ እንዴ ብዙ?
አልፎ አልፎ ነዉ..እምብዛም ተከታታይ አይደለሁም፤ነገር ግን ማንቸስተር እና ባርሴለናን በአይኔ አይቻቸዋለሁ፤ደቡብ አፍሪካ ለስራ ሂጄ ነዉ ያየሁዋቸዉ..
—ታድያ ሀሳቡ እንዴት መጣልህ?
እኔ በኛ ቤተ-ክርስተያን ስብከተ ወንጌል ዉስጥ አለሁበት፤እናም ሀገሬ ወደ ብራዚል እንድትሄድ በጣም እፈልጋለሁ፤ስለሆነም አሰብኩበት እና ለሰፈሬ ልጅ አስራት መገርሳ ነገርኩት፤በጣም ደስ አለዉ..እናም ለአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ነግሩዋቸዉ ፍቃደኛ ሁነዋል፤አርብ ጥዋት ይህንን ለማድረግ አስበናል፤አልያም እነሱ ባመቻቸዉ ጊዜ ከጨዋታዉ በፊት ሊሆን ይችላል፤
—ናይጄሪያ ዉስጥ በሴኔት ደረጃ ይህንን አስበዋል፤ምናልባት ሁሉም ሰዉ ሲጸልይ ..ጨዋታዉ ወደ ጸሎት ፉክክርነት….
አይ እኔ በአንድ ነገር አምናለሁ፤መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ የሚል ነገር አለ..ከናንተ መሀል የየዋሁን ጸሎት እቀበላለሁ ይላል፤ስለሆነም ሁላችንም በጥሩ መንፈስ ጸልየን አምላክ ሊሰማን ይችላል፤እናም እሱ ያሸንፋል፤
—የሌላ እምነት ተከታዮችስ እንዴት አሰባችሁ
ሁሉም ሰዉ በየሀይማኖቱ ቢጸልይ ጥሩ ነዉ፤እናም ቀና የሆነ ሰዉ ሁሉ ምንም እምነት ይኑረዉ ጸሎቱ ይሰማል አለኝ፤
አክሊሉ በንግድ ስራ ነዉ የሚተዳደረዉ–ከቻለኩኝና ትኬት ካገኘሁ እሁድ ስታድየም እገባለሁ፤ካልሆነ ግን በጸሎት ቡድኑን እንደግፋለን ብሎኛል፤

ይሄ የኢትዮጵያና ናይጄሪያ ጨዋታ ጡዘቱ ላይ የደረሰ ይመስላል፤

No comments:

Post a Comment