Thursday, October 17, 2013

በአፍሪካ ዋና ከተማ 24 ሰዓት ውሀ የሚያገኘው 65 በመቶው ህዝብ ብቻ ነው

ጥቅምት (ሰባት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የውሀ ቀለም አይቶ የማያውቅ ህዝብ አለ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ 65 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሀ 24 ሰአት እንደሚያገኝ ገልጸው፣ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት 5 ቀናት፣ ከ10-15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት አንድ ቀን ውሀ ያገኛል ብለዋል።
በአብዛኛው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች የውሀ አቅርቦት ከ75 እስከ 99 በመቶ ይደርሳል። የአፍሪካ መዲና እየተባለች በምትጠራዋ አዲስ አበባ የሚኖረው  ከ35 በመቶ በላይ ህዝብ ሳምንቱን ሙሉ ውሀ አያገኝም መባሉ የ11 በመቶውን እድገት ዜና ጥያቄ ምልክት ውስጥ መክተቱን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ1 ሚሊዮን 500 ሺ በላይ በላይ ህዝብ የ24 ሰአት ውሀ ተጠቃሚ ካልሆነ በገጠር ኢትዮጵያ አለው ሁኔታ ምን ሊመስል ነው የሚል ውይይት መክፈቱን አዲስ አበባው ዘጋቢያችን  የላከው ሪፖርት ይጠቀሳል።

No comments:

Post a Comment