አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤውን በሸራተን አዲስ እያካሄደ ነው።
ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየም ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በነገው ዕለት ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአማራ ክልልን ወክለው በዕጩነት የቀረቡት አቶ ተካ አስፋው ራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል።
አቶ ተካ ዕጩ አድርጎ የላካቸውን የአማራ ክልል አመስግነው ፤ ይህን ውሳኔ ሲወስኑ ባለማሳወቃቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።
የፌዴሬሽኑ ቀጣይ ፕሬዝዳንት በነገው ዕለት በሚደረገው ምርጫ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment