Wednesday, August 21, 2013

የፍቼዉን የአንድነት ሰልፍ የሚያስተባብሩ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ተደበደቡ

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ የአንድነት ፓርቲ የሚያደርጋቸዉን፣  አገረ ሰፊ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎቹን በስፋት ገፍቶበታል። በኦሮሚያ በሚገኙ ሶስት ታላላቅ ከተሞች፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ባሌ ሮቢና ፍቼ ሰላማዊ ሰልፎች እንደሚያደርግ፣  ለከተሞቹ ባለስልጣናት ያሳወቀ ሲሆን ፣ ቅስቀሳዎችንም በስፋት አያደረገ ነዉ።
ከጥቂት ሰዓታት በፊት ፣ ሰላማዊ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ፍቼ ያቀኑ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አሰተባባሪዎች በአገዛዙ ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፣ ከወዲሁ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠዉን የዜጎች መብት ለመርገጥ ኢሕአዴግ እየሰራ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነዉ። የፓርቲዉ አመራር አባላት በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት መግለጫ እንደሚሰጡም ለማወቅ ችለናል።
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጂንካ ሰላማዊ ሰልፎች በወላይታ ሶላማዊ ሰልፎችን፣ በአዲስ አበባና በወላይታ ሶዶ ደግሞ  የተሳኩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማድረጉ ይታወቃል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6599

No comments:

Post a Comment