Friday, August 23, 2013

የልማታዊ ጋዜጠኞች አንዝህላልነት እና የአብርሃ ደስታ እማኝነት “የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች “

ከነብዩ ሲራክ
ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ግፍ ተፈጸሞባቸው ወደ ባገር ቤት የሚሸኙ እህቶች የመኖራቸው መረጃ ደረሰኝ ። በተለይም በቅርብ እከታተላቸው የነበሩ አህቶች እንግልት በመጠቆም በዚው በፊስ ቡክ የማለዳ ወግ ዳሰሳየ ላይ አንድ መልዕክት አስላልፊ ነበር! መልዕክቱም ለልማታዊ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች ሲሆን የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ ” የምንናገረውን ማመን መቀበል አቅቷችሁ እንደ ጠላት ከምታዩን ረቡዕ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሂዱና ከፍተኛ ግፍ ተፈጸደሞባቸው ከሳውዲ ተጠርፈው ወደ ባገር የሚገቡትን የኮንትራት ሰራተኞችን ተመልክቱ !”የሚል ነበር።
ንቁ እዝነ ልቦንና ያልታደሉት ልማታዊ ጋዜጠኞች በቦታው ሄደው ከቤሩት የተመለሱትን ሻንጣ የደረደሩ እህቶች በቴሌቪዥኑ መስኮት ብልጭ አድርገው ከማጥፋታቸው ባለፈ ከሳውዲ ያለጫማና የረባ ልብስ ተደብድበውና ተደፍረው የተመለሱትን ግፉአን ሊያሳዩን እንኳ አልፈቀዱም! ጋዜጠኞቻችን አልተሳሳቱም!!! የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ያን ሰሞን “ስደት ይቅር ” ምንቴስ ሰፊ ሽፋን በየሚዲያው እየሰጡ ፣ የደበቁትን መከራችን እያሳዩ እያሉ ህዝበ አዳም ፣ ሃገሬውን ሲያስለቅሱን የከረሙት ወደ ነፍሳቸው ተመልሰዋል ብየ በማሰቤ ስህተቱ የእኔ ግምት ነው!!! ጉዳታችን እዩት ቀሪው እንዲማርበት ፣ ሃላፊዎቻችን ይዩትና ወደ ዘነጉት የዜጎች ጉዳይ ያተኩሩ ዘንድ የተገፊ ግፉአኑን ጉዳይ ተከታትየ መጠቆሜ በአደባባይ ቃል የገቡትን ይፈጽማሉ ብየ በማሰቤ የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ስህተቴ አንድና አንድ ነው!!! የአረብ ሃገሩን የስደት መከራ የሚፈልጉት ለፕሮፖጋንዳ እንጅ ቀሪውን ማስተማርን እንደልሆነ አለማሰቤ ነው ስህተቴ ! በእንዝህላል ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን አዝኘም ብቻ ሳይሆን አፍሬ ዝም ማለቴ ግን እውነት ነው! ዛሬ ማለዳ ግን መልካም መረጃም የሚየ ስፈነጥዝ ባይሆንም መረጃው በመሰራጨቱ የተደሰትኩበትን መጣጥፍ ተመለከትኩ ።
ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ከአረብ ሃገር ወደ ሃገር የገቡትን እህቶች አብርሃ ደስታ አግኝቷ እንዳነጋገራቸው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ካስተላለፈው መልዕክት ለመረዳት በመቻሌ ደስ አለኝ ! በገዥው የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር ላይ በተለይም ስለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመቀሌ ሆኖ በሚያሰራጫቸው የሰሉ ሚዛናዊ ሂሶች ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው አብርሃ ድስታ ግፉአን እህቶቸችን ቦሌ አየር ማረፊያ አግኝቷቸው ያየውን የሰማውን እጥር ምጥን ባለው የለመድነው መረጃ አቀባበል እንካችሁ ብሎናል ። የአብርሃ እማኝነት አስደስቶኝ እኔም ለዛሬ ወግ ዳሰሳ አበቃሁት ! ወዳጃችን አብርሃ ደስታ ሆይ ! የአረብ ሃገሩ የብዙሃን የኮንትራት ሰራተኞች አስከፊ ህይዎት ያጫዎቱህ ወደ ሃገር ለመግባት የታደሉት መሆናቸውን አስረግጨ እነግርሃለሁ ! ያየሃቸው የታደሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው ! የመንግስት ተወካይ አለን ለማለት አልደፍርም ! እውነቱ ይህ ነው ! አንተም እንኳን ከግፉአኑ ሰምተህ አሰማህን ! ይህ የማናችንም ሃላፊነት መሆን ሲገባው እያደረግነው አይደለም! የእህቶቻችን ህይዎት በአረብ ሃገር ምስክርነቱ ይህ ነው ! እንዲህ ይኖራል ! የእኔን በዚህ ላብቃና እጥር ምጥን ወዳለችው የአብርሃ ደስታን እማኝነት ከዚህ በታች እንድትመለከቱ ስጋብዝ ለአብርሃ ምስጋና በማቅረብ ጭምር ነው! እነጰ አበቃሁ ! ቸረወ ያሰማን !
ነቢዩ ሲራከ
By Abraha Desta የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች ——————————————— ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ጠዋት ቦሌ ኤርፖርት ነበርኩ። ኢንተርናሽናል ተርሚናሉ ከዓረብ ሀገራት በተመለሱ እንስት ኢትዮዽያውያን ተጥለቅልቋል። የተከፉና የተረበሹ ይመስላሉ። ከሰዓት በኋላ ወደ መቐለ ለመመለስ ወደ ሀገር ውስጥ ተርሚናል ገባሁ። ከነዚህ ጠዋት ረጅም ሰልፍ ይዘው ያየኋቸው ተመላሾች የተወሰኑ አገኘሁ። ስለ ህይወታቸው፣ ስለሚደርስባቸው እንግልት ወዘተ አጫወቱኝ። በዓረብ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እንደሰው አይቆጠሩም፤ ብዙ አካላዊና ስነ አእምራዊ ችግር ይደርሳቸዋል። ብዙዎቹ አብደዋል፣ ራሳቸው አጥፍተዋል። ኢትዮዽያውያን በመሆናቸው ራሳቸው ይረግማሉ፤ በመፈጠራቸው ያዝናሉ። የኢትዮዽያ ኤምባሲ ግን ምንድነው የሚሰራው? የዜጎች ደህንነት መጠበቅ’ኮ የመንግስት ሐላፊነት ነው። የኢትዮዽያውያን ስደትና ግፍ ሀገራችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊመራት ይችላል።
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6634

No comments:

Post a Comment