By Mesfin.H
የነገሩ መነሻ አቶ ሀ/ማርያም የሙስሊም ወገኖቻችንን መንግስት መረዎቻችንን ይፍታ፤ የሀይማኖት ነፃነታችንን ያክብርልን እና
መንግስት ከሀይማኖት ጣልቃ ገብንት ይታቀብ ብለዉ
ላነሱት ጥያቄ የአክራሪነት፤ የፅንፈኝነት ጎራን የተከተሉ የጥፋት ሀይሎች፤ እያሉ ዋልታ ለተባለዉ መረጃ መአከል የሰጡትን ቃለመጠይቅ በመሰማቴ፤ አካሄዳቸዉ በጣም አደገኝ
እንደሁነ ስለገባኝ እኚህ ሰዉ የሚመክራቸዉ የቅርብ የሚሉት ሰዉም
የላቸዉም እንዴ ብዬ ከምር አዘንኩ፡፡
ዕደዉም ድሮ አያቴ ሲነግረኝ
በነሱ ዘመን በንጉሳዊ የአገዛዝ ስርአት
መሪዎች ህዝብ ጥየቄዉ ምንድን ነዉ? የልቡስ ሀሳብ ምነድን ነዉ
የሚለዉን ጥያቄ፤ በበታች ሹማምንታቸዉ በኩል ወርደዉ ሕዝቡን ይጠይቁ
እንደነበር እና በተጨማሪም እረኛስ ምን ብሎ ዘፈነ በለዉ ይጠይቁ ነበር አለ፡፡ ምክንያቱም እረኛ እቤት ዉስጥ የሚሰሙ የህዝብ ብሶቶች በዘፈን አደባባይ
ያወጡታል ነበር ያለኝ አያቴ፡፡ ያንንም በመስማት አነሰም በዛ አስተዳደራዊ ማስተካከያ ያደርጉ ነበር አሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ የዘመኑ ሚንሰትር እንደ ሗዋላ ቀሩ አስተዳደር እንኮዎን ሀገር መምራት ተስኖወዋቸዉ ህዝብን ለእንግልት ፤ ለሞት ዳርገዉታል፡፡
ታዲያ እንደ አለመታደል ሆኖ አቶ ሀ/ማርያም ህዝብ ምን
ይላል? የህዝብ ጥያቄ ምንድን ነዉ? ለሚለዉ ጆሮ የላቸሀዉም ወይም ሊሰሙ አይፈልጉም፡፡ በተቃራኒዉ በሀይማኖቱ ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረን ህዝብ ሆድና ጀርባ ለማድረግ
ከተቻለም የሀይማኖት ችግር በሀገራችን እንዲነሳ አደገኛ መርዛቸዉን
እየረጩ ይገኛሉ፡፡ለነገሩ ወያኔዎች እንደሚያስቡት አይሳካላቸዉም ህዝብ ነቅቶባቸዋል ቢሁንም ግን ሁላችንም
በተቻለዉ መንገድ በነሱ መንገድ እንዳንሄድ እንጠንቀቅ ትግላችንን
አጠናክረን እንቀጥል፡፡
ግን ግን እኛ ኢትዮያዉያን ከመሪዎቻችን እስከመቼ ነዉ እንደ አይጥና ድመት እየተፈራራን ጠላት ሆነን
የምንኖረዉ? መቼ ነዉ? መሪዎቻችንን በፈቃዳችንን በስልጣን ላይ ምናስቀምጣቸዉ ሳንፈልጋቸዉ የምናወርዳቸዉ፡፡
የሀገራችን ገዢዎች እንደ ሰለጠኑት ሀገር ባለስልጣናት
ህዝብን የሚፈሩበት እና የሚያከብሩበት፡ ዘመን መቼ ይሆን?
ትክክል መስሎአቸዉ አቶ ሀማርያም በጥፋት መንገድ
በጨለማ እየሄዱ ነዉ፡: በዚህ ሁኔታ እረጅም ጉዞ መሄድ የሚችሉ አይመሰለኝም፡፡ ይልቁንም ወደ ቀደመዉ ስብእናቸዉ በመመለስ
ለወያኔ የጥፋት ተልእኮ መጠቀሚያ ከመሆን እነዲታቀቡ እመከርሆታለሁ፡፡ የሙስሊሙን ጥያቔ ያለእንዳች ቀድመሁኔታ ይመልሱ::
የፖለቲካ እስረኞችን እና ጋዜጠኞችን በፍጥነት ይፍቱ፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ
ያለወያኔ አሸባሪ ስለሌለ ህዝብን ማሸበር በፍጥነት ያቁሙ፡፡ ያለበለዚያ ታሪክ የማይሽረዉ ስህተት ሰርተዉ ያልፋሉ፡ ለነገሩ አሁንም
ከታሪክ ተያቂነት አሁንም አላመለጡም፡፡ ብቻ አሁንም ሌላ ስህተት
ዉስጥ ባይገቡ ይሻልዎታል፡፡ የሚስኪኖች፤ የንፁኀን፤ የህፃናት፤ የባልቴት፤ የአረጋዊ እና የወጣቱ እንባ ይፋረዳቹሀል፡፡ የህዝብን ጥያቄ በጉለበት ማፈን አትችሉም፡፡
No comments:
Post a Comment