August 20, 2013

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሃዲያ መሀመድ ከ18 ቀን እስር በኋላ በ10,000 ብር ዋስ ተለቀዋል፡፡ አንድት በወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ እንዲጨናገፍ የተለያዩ የውንብድና ድርጊቶችን ሲፈፅም የነበረው የዞኑ የዞኑ አስተዳደር ወ/ሮ ሃዲያ መሀመድን “አንድነት ፓርቲ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለአመፅ የሚቀሰቅስ በራሪ ወረቀት እንድበትን ተልዕኮ ሰጥቶኛል” ብለው እንዲመሰክሩ ጫና ቢያደርግባቸውም ባለመስማማታቸው ለ18 ቀናት በእስር እንዲማቅቁ አድርጓቸዋል፡፡
*ፎቶዎቹ ወ/ሮ ሃዲያ መሀመድ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት የተነሱ ናቸው፡፡


No comments:
Post a Comment