አንድነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። አገዛዙ ግን ሕገ መንግስቱን በመርገጥ የሰለጠነን ሳይሆን፣ የዛቻን ፖለቲካ እያራገበ ነዉ።
«በሮቢ ደም ሊፈስ ይችላል»
በማለት ማስፈራሪያዊች እየቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊሲስ ሰልፍን የምታደርጉ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቀዋል።
የሮቢ የአገዛዙ አስተዳዳሪዎች፣ 20 ሰዎች የሚገኙበት የ«ሽማግሌዎች» ቡድን አቋቁመዋል። ይሀ ቡድን ከጥቂት ሰዓት በኋላ ከሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ጋር ዉይይት ያደርጋል።
ኮምቴዉ፣ ስብሰባው ከተደረገ ብጥብጥ ተፈጠሮ ደም ሊፈስ እንደሚችል ስጋት ያላቸው ይመስለላል። ነገር ግን በስብሰባዉ የግብረ ኃይሉ መሪዎች ሰልፍ ሰላማዊ እንደሆነ ለማሳመን እንደሚሞክሩ ሰልፉን ለመሰረዝ ፍቃደኛ እንዳለሆኑ ያሳዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ፖሊስ፣ «ሰልፉ ሕገ ወጥ ስለሆነ፣ አስፈላጊዉን እርምጃ እንወስዳለን » የሚል ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ ለአንድነት አመራሮች የሰጠ ሲሆን፣ የፓርቲው አመራሮች ግን፣ የፖሊስን ማስፈራሪያ ዉድቅ አድርገዉታል። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት እንደሆነ የገለጹት አንድነቶች፣ ሰልፉ በታቀደበት ቀን እንዳይደረግ ከተፈለገ፣ ፖሊስ ምክንያቶችን በመስጠት እንዲራዘም የመጠየቅ እንጂ፣ ሕገ መንግስቱን በመናቅ የዜጎችን መብት መዳፈር እንደሌለበት አሳስበዋል።
No comments:
Post a Comment