Saturday, August 31, 2013

አዜብ መስፍንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ግምገማ እና ጥናት በይፋ ተጀምሯል::

ምንሊክ ሳልሳዊ

በወያኔ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የሆነውን እና ለመለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው አዜብ መስፍን ቅርብ የነበረውን እንዲሁም የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ አቶ ዘርኡ አንገታቸው በስለት አሳርዶ፣ የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነው በገመንድ አንቆ..የገደለ እና ብዙ ወንጀሎች የሰራው በሙስና የተዘፈቀው ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ መንገዶች ሁሉ ወደ ወይዘሮ አዜብ እያመሩ መሆናቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::

ይህ በሙስና እና በጭካኔው ወደር ያልተገኘለት የሕወሓት የደህንነት አናት በበቀለኛው በአቶ ስብሃት ቡድን በኩል በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ከስልጣን ወርዶ ከቆየ በኋላ ስልታንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት በሚል ተወንጅሎ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::ይህ ግለሰብ በአሁን ወቅት በወህኒ ቤት ከሚገኘው ከቀድሞው የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ድይሬክተሩ እብሪተኛው ገብረዋሃድ ወልደጊዮርጊስ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ወዳጅነት እና ቅርርብ ያለው ሲሆን ገብረዋህድ በበኩሉ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የተለየ ግንኙነት የነበረው እና አስተማሪዋ የነበረ ሲሆን ለዚህም ስልጣን ያበቃችው እሷ እንደሆነች ሲታወቅ የጸጥታ ሹሙ በቁጥጥር ስር መዋል ወይዘሮ አዜብን ለመያዝ እሳቤ ያደረገ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል::
ወይዘሮ አዜብ መስፍን በቅርቡ የተላያዩ የህወሓት ድርጅቶችን በጋራ ከሚመራው ኤፈርት ተብሎ ከሚጠራው ድርጅት ስራ አስኪያጅነት መውረዳቸው የታወቀ ሲሆን በስልታን ዘመናቸው ድርጅቱ ኦዲት የሂሳብ ምርመራ ተደጎለት የማያውቅ እና ለመንግስት አስፈላጊውን ግብር እና ሪፖርትም ጭምር ያልሰጠ በመሆኑ በቀድሞው ስራ አስኪያጅ ላይ የቀረበው ክስ ወይዘሮ አዜብንም የሚጠብቃቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም የተመዘገቡ ቀረጥ መከፈል ሲገባቸው ያልከፈሉ ጨረታ በዝምድና ሳያሸንፉ የሚወስዱ አላግባብ የሚበለጽጉበት ሁኔታዎች በምርመራ መገኘታቸው በባለቤታቸው ስም እና ዝና ለመነገድ መሞከራቸው ከፓርቲው ውጪ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ሴትየዋ በአቶ ስብሃት ቡድን ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል::
ወይዘሮዋ ባለበታቸው በነበረበት ሰአት ከከፍተኛ ደረጃ የሚፈሩ እና ፓርቲውን ለመዘወር በየስብሰባው አደገኛ ቃላቶችን የሚናገሩ የነበሩ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የአሁኑ የደህንነት ሹም ወንጅለውት ከስልጣን በማውረድ አሁን ወደ ወህኒ የወረዱትን ወልደስላሴን ማሾማቸው ይታወቃል::የስበሃት ቡድን ደጋፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ በዚህ ጉዳይ ቂም ቋጥረው መለስ ከሞቱ በኋላ እስከዛሬ ድረስ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የጎሪጥ እንደተያዩ ነው::

በአንድ ወቅት እብሪተኛ እና የሃያልነት ስልጣን በእጇ የነበረው አዜብ ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ቀስ በቀስ በፖለቲካ ባላንጣዎቿ እየተገፋች ዋጋቢስ እየሆነች መታለች::በአሁኑ ወቅት አዜብ ምንም አይነት ስራ የሌላት እና ቤት ውስጥ ተቀምታ የምታሳልፍ የፖለቲካ ቁማር የተበላሽባት ወይዘሮ ሆናለች::ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት በችሎታ ማነስ እና በሙስና ከኤፈርት የተባረረችው አዜብ በእፈርት ስር የሚተዳደሩ ሰራተኞች ከፍተኛ የሆነ ስሞታ ሲያሰሙባት እና ሲከሷት እንደነበር ይታወቃል::

ምንጮቹ እንዳመለከቱት ወይዘሮ አዘብ በአባይ ወልዱ በሚመራው የሕወሓት አንጃ ውስጥ በረከት ስምኦንን አስከትላ እየተንቀሳቀሰች ሲሆን መሰረቱን መሃል አዲስ አበባ ላይ የተከለው እና ማእከላዊ መንግስቱን እንዳሰኘው የሚያሽከረክረው በደብረጺሆን እና በደህንነቱ ሹም ጌታቸው የሚመራው ሌላው የሕወሓት አንጃ ስብሃት ነጋን አስከትሎ "ብረታሙ" በሚል መጠሪያ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ::ይሀ ብረታሙ እያለ ራሱን የሚጠራው የሕወሓት አንጃ የጸረ ሙስናን ዘመቻውን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ወይዘሮዋ ቤተመንግስት በነበሩ ጊዜ የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ሙስናዎች እና ተግባራት ለፍትህ ለማቅረብ አስፈላጊውን ጥናት እና ግምገማ እያደረገ ነው ሲሉ ምንጮች መረጃውን ሰተዋል::                   ምንሊክ ሳልሳዊ  Vs Based onኢትዮሚዲያ 

1 comment:

  1. Sooner or later truth triumphs and all looters and Killers will face justice.

    ReplyDelete