Saturday, August 31, 2013

የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

   http://www.ethiopianreporter.com
የፌዴራል የሥነ ምግባር የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉትን የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩትን አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤልን፣ ከነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ አስሮ በመመርመር ላይ ይገኛል፡፡
አቶ ወልደ ሥላሴ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ድርጊት የመረጃና ደኅንነት ኃላፊ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት በሥልጣናቸው ያላግባብ በመገልገልና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርተዋል በሚል መሆኑን፣ የኮሚሽኑ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ 
የኮሚሽኑ መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የሚቀረው ምርመራ እንዳለው ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት በዝርዝር አስረድቶ፣ ለተጨማሪ የምርምራ ጊዜ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡
አቶ ወልደ ሥላሴም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም፣  ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ግራና ቀኝ ካዳመጠ በኋላ፣ የተርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ የመርማሪ ቡድኑ ጥያቄን ተቀብሎ፣ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዶለታል፡፡ ለጳጉሜ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

No comments:

Post a Comment