Monday, September 2, 2013

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሙስሊም ባለስልጣናቱ ላይ ሊዘምት ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ

ሙስሊም የኢሕኣዴግ አመራሮች:- ብዝኃነትን በአግባቡ ለማስተናገድ የቆረጠውን ሥርዓት በተሳሳተ አድራጎታቸው የሚፈታተኑ መንግሥታዊ አገልግሎትን ሃይማኖታዊ መልክ የሚያሲዙ አክራሪዎችን የሚደግፉ ሲል ወንጅሏቸዋል::
በወያኔ የፌዴራል ሚኒስቴር እና በተለጣፊው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዬ የተሰራውን ጸረ-እስልምና ጉባዬ እና ሰልፍ በሚገርም አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ገዢው ፓርቲ የደረሰበትን ኪሳራ ለመሸፈን በሙስሊም ባለስልጣናቱ ላይ የበቀል እርምጃ ሊወስድ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: 

የህሊና እና የሞራል ስልጣናቸውን በዘነጉ የሃይማኖት መሪዎች ዲስኩር የተችሞነሞነው የጸረ አክራሪነት እና አሸባሪነት ጉባዬ የተጠበቀውን ያህል ውጤት እንዳላመጣ የሚናገሩት የፌዼራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን በሰጡን መረጃ መሰረት ይህ ጉባዬ የገዢው ፓርቲ ደፋ ቀና ብሎ ያዘጋጀው በቀጣይነት እርምጃ መውሰድ በሚፈልግባቸው አካላት ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ እንጂ የጸረ አክራሪነት እና አሸባሪነትን የማውገዝ ምንም አይነት ግብ እንዳሌለው ሲናገሩ ወያኔ ያቀረበው ንድፈ ሃሳብ እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባዬ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እና የገዢው ፓርቲ ያጼረው ነው ሲሉ ጠቁመውናል::

ብዙ ለመናገር ያልደፈሩት ምንጮች እንዳሉት የፌዴራል ሚኒስቴር ኤሽስፐርቶች እና የደህንነት ቢሮ ሃላፊዎች በመጪው ሊወሰድ የሚችለውን የሙስሊም ባለስልጣናትን ጉዳይ እንዲሁም የሃይል እና የረቀቀ እርምጃ ላይ የሕወሓት ንድፈ ሃሳብን መሰረት አድርገው ውይይት መጀመራቸውን እና ቀጣይ ሂደቶችን ለከፍተኛ የፓርቲ ባለስልጣናት ሪፖርት እንደሚያቀርቡ እና እንደሚያስወስኑ እየተጠበቀ ነው::



ይህንን የሙስሊሙን መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቄ ለማጨናገፍ ህገ መንግስቱን እንደመነገጃ የተጠቀመበት ሕወሓት መራሹ ጁንታ በፓርቲው እና በመንግስቱ መዋቅር ውስጥ አሸባሪነትን እና አክራሪነትን በመጠቀም ህግን የጣሱ ባለስልጣናት አሉ በሚል ሰበብ ሙስሊም ባለስልጣኖችን የወያኔ አብዮት ሊበላ መሆኑ ተሰምቷል::የብዙሃኑን መብት እና እኩልነት ለመናድ ሞክረዋል ያላቸውን ሙስሊም ባለስልጣናትን በተለያዩ ወንጀሎች የፈረጃቸው ሲሆን በአመራር ደረጃ ላይ ያስቀመጥናቸው አክራሪነትን የሚያበረታቱ ባለስልጣናት በሌላው እምነት ተከታይ ላይ በደል እየፈጸሙ ነው በሚል በሌሎች ጥርስ ውስጥ ለማስገባት ሞክሯል::
ሕወሓት ሙስሊም ባለስልጣኖቹን ሊበላ በመፈለጉ ሰበብ ሲፈጥርባቸው መንግስት እና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን እያስተማርናቸው(?)ለሙስሊም አክራሪዎች እና አሸባሪዎች ድጋፋቸውን በመስጠት የብዙሃኑን መብቶች በተግባር እያረጋገጠ ያለውን ስርኣት በተሳሳተ አድራጎታቸው ተፈታትነዋል ሲል ወንጅሏቸዋል::

ሃይማኖታዊ አዝማሚያ ባልተለያቸውና በመንግሥታዊ ኃላፊነትና በእምነታቸው መካከል ያለውን ልዩነት በውል መገንዘብ የተሳናቸው ኃላፊዎች ደግሞ የራሳቸውን ስህተት ሲሠሩ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡ መንግሥታዊ አገልግሎትን ሃይማኖታዊ መልክ ማስያዝ፣ የእምነት ማድረሻ ተቋማት ግንባታን ከሃይማኖትህ በመነሳት መፍቀድና መከልከል፣ ሙስሊም አመራር ሆኖ የአስተሳሰብ ችግር ያለበት በሚያስተዳድርበት አካባቢ ክርስቲያን ዜጎችን የሚበድሉ ሥራዎች መሥራት የሚስተዋል ችግር ነው በማለት ክርስቲያኑን ለማወናበድ ንጹሃን ሙስሊሙችን ለማስደንገጥ ሙስሊም ባለስልጣኖቹን ለመጥረፍ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተጣደፈ ነው::
source: Minilik Salsawi

No comments:

Post a Comment