Friday, January 17, 2014

“ጎል አለማግባተችን እንድንሸነፍ አድርጎናል—ስራ ፈት መሆን ስለማልፈልግ ከአሰልጣኝነቴ አለቅም”…ሰዉነት ቢሻዉ


Photo

ስለጨዋታዉ እና ሌሎች አስተያየቶቸ በኋላ እንመለሳለን፡፡ሰዉነት ግን ከጨዋታዉ በኋላ ይህንን ብለዋል፡፡ ዛሬ ጥሩ ነበርን ፡-ከመጀመሪያዉ ጨዋታም ተሽለናል፡፡ነገር ግን ያገኘናቸዉን አጋጣሚዎች ባለመጠቀማችን እንድንሸነፍ አድርጎናል አሉ፡፡ ስለቡድኑን መልቀቅ ተጠየቁ…እኔ እለቃለሁ አላልኩም፡፡ለመልቀቅም አልፈልግም፡፡ፌዴሬሽኑም ልቀቅ አላለኝም፡-በራሴ መልቀቅ አላሰብኩም፡፡ምክንያቱም አሁን ስራ አለኝ፤፤ከለቀቅኩ ግን ስራ ፈት እሆናለሁ፡፡ስራ አጥ መሆን ደሞ አልፈለግም ብለዋል፡፡ ከቻን ስለመዉጣታቸዉ …እኛ ዋና ግባችን ልምድ ማገኘት ነበር፡፡እሱን ከቻን ዉድድር እያሳካን ነዉ አሉ!! ዛሬ ዋልያዉ ጨዋታዉን ከጨረሰ በኋላ ሰዉነት ከፍተኛ ተቃዉሞ ከደጋፊዎች ገጥሞዋቸዋል፡፡በተለይ ጨዋታን አንብቦ በመቀየር ድክመት ተተችተዋል፡፡የዉሀ ላስቲክም ተወርዉሮባቸዋል፡፡ካፍ በመጀመሪያዉ ጨዋታ ይህ ነገር እንዳይደገም አስጠንቅቆ ነበር፡፡እናም ቅጣት መኖሩ አይቀሬ ይመስላል፡፡
Source:http://www.ethiotube.net/

No comments:

Post a Comment