
አስገራሚዉ ነገር በዛዉ የካፍ ጋዜጠኞች ይለፍ የመጡ 4ት ጋዜጠኞች ምንም ሳይጠየቁ ዛሬ ገብተዋል፡፡ትላንት እነ ፍስሀ የታሰሩበትን ይለፍ ዛሬ ሰርትዋል፡፡ፎቶ አንሺዉ ደመቀ ግን ለጥቂት አልተሳካለትም፡፡የእስሩን ነገር ፈርቶ ፎቶ እያነሳ የሚግሬሽኑን ቦታ አለፈዉ፡፡እናም ያለምንም የመግቢያ ቪዛ የደቡብ አፍሪካን ምድር ረገጠ፡፡ግን ቆይቶ ልክ እንደሱ የወረቀት መግቢያ የያዙ ጋዜጠኞች ሲያልፉ አየና እሱም ተመልሶ ለማስመታት ሲሄድ ተያዠ፡፡እንዴት ሳታስመታ ገባህ በሚል አሁንም ድረስ እዛዉ እስር ላይ ነዉ፡፡
ዋልያዉ ጥቂት በሚባሉ ኢትዮያዊያን አቀባበል ተደርጎለታል፡፡የዣሬ አመት የኦሊቨር ታምቦ አይሮፕላን ማረፊያ ከመጡ ኢትዮጲያዊያን ጋር ሲነጻፀር ቁጥሩ እጅጉን አንሰዋል፡፡ይህም ዛሬ ተጫዋቾቹን ለማግኘት ጥሩ አጋጣሚ ሁንዋል፡፡ከጆበርግ ወደ ዉድድሩ ስፋራ ብሎምፎንቴን 400ኪሜ ርቀት አለ፡፡እናም ዋልያዉ 12 ሰአት ላይ ከጆበርግ ወደ ብሎምፎንቴን የ40 ደቂቃ በረራ አድረጎ ፕሮቲያ ሆቴል አርፍዋል፡፡እዚሁ ሆቴል የኮንጎ ቡድን ያርፋል፡፡ነገ እንደሚገቡም ይጠበቃል፡፡
የመጀመሪያዉን ልምምደ ነገ ጥዋት እንደሚደረግ ታዉቅዋል፡፡የተከላካዩ ቶክ ጀምስ ሻንጣ ጠፍትዋል፡፡ከጆበርግ አይሮፕለኑ ሲነሳ የቶክ እቃ አልተጫነም ነበር፡፡የቡድን መሪዉ ዮሴፍ እቃዉን ለማስመጣት ጥረት ያደረገ ነዉ፡፡የዣሬዉ ጉዞ ብዙ ተጨማሪ ነገሮች አሉት፡፡አሁን በጣም ስለመሸ ነገ እንቀጥልበታለን፡፡
# by Saied Kiar#
No comments:
Post a Comment