Friday, January 17, 2014

የአፅቢ ግጭት (ክፍል ስድስት) ወታደሮቹ ህዝብ እንዲበተን ጥሪ አቀረቡ


በሰባት መኪኖች ሙሉ ተጭነው ወታደሮች ገብተው አከባቢው ተቆጣጥረውታል። "የዞን አስተዳዳሪዎች ነን" ያሉ ባለስልጣናት ህዝቡ "የአሸባሪነት ተግባር" እያከናወነ መሆኑ በርቀት ተናግረዋል። ህዝቡም "አሸባሪዎች እናንተ ናች ሁ፤ ልጆቻችን ፍቱልን" እያለ ሲጮህ ነበር። በመጨረሻም ወታደሮቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስጠንቀቅያ ቢሰጡም አራቱ የአፅቢ ወንበርታ ልጆች ካልተፈቱ እንደማይበተን አስታውቀዋል። መከላከያውና አስተዳዳሪዎቹ ቢያስፈራሩም ህዝቡ ግን ለመበተን ፍቃደኛ አልሆነም። ዘጋቢዎቼ ወደ ቤታቸው እየተንቀሳቀሱ ነው። ነገ እንገናኝ። አሁን ከምሽቱ 3:55 ነው። ቸር ያሰማን።
Source:Abraha Desta

No comments:

Post a Comment