Thursday, January 16, 2014

የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ያነጋግራሉ

Sunday school Mezemeranሐራ ዘተዋሕዶ. | January 16th, 2014


የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲኾን የሚጠይቁት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ አጠቃላይ ብዛት ያላቸውን የሀ/ስብከቱን ወጣቶች የሚወከሉና ከ140 ሰንበት ት/ቤቶች የተውጣጡ ናቸው፡፡
  • በሀ/ስብከቱ፣ በክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅርና አደረጃጀት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶችን
  • በሀ/ስብከቱ፣ በክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅርና አደረጃጀት ውስጥሰንበት ት/ቤቶችን በማደራጀትና በማጠናከር ተልእኳቸውን እንዲወጡ ማድረግ ከዋነኛ ዓላማና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡
  • የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ በማፋጠን፣ የቤተ ክርስቲያንን ኦርቶዶክሳዊ ማንነትና አስተዳደራዊ አንድነት በመጠበቅ፣ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን በመከላከል፣ ሞያዊ አስተዋፅኦን ለቤተ ክርስቲያን የማበርከት ድርሻ ያላቸው የአያሌ ተሰጥኦዎች ባለቤት የኾኑ ሰንበት ት/ቤቶች በአባቶች እግር ላላቸው የተተኪነት ሚና ተጨባጭና ቀጣይ እንዲኾን ዋስትና ነው፡፡
  • የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነዱ በፋይናንስ ፖሊሲውና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው÷ የቤተ ክርስቲያናችን የገንዘብ አያያዝና አሠራር ግልጽነትና ተቀባይነት ያለው እንዲኾን ማድረጉ መሠረታዊ ተልእኮዋን ለማጠናከር ከሚኖረውአጠቃላይ ፋይዳ ባሻገር በዋና ተግባርነት ደረጃ ያስቀመጠው የሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት የሙዓለ ንዋይ ምደባ (budgeting or financial arrangements) በቂ የፋይናንስና በጀት ድልድል እንዲያገኝያስችላል፡፡
  • ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ምሥረታ የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚጠቁመው 65 ዓመታትን ባስቆጠረው የዘመኑ የሰንበት ት/ቤቶች አሠራር የታቀፈው ወጣት 70% የምእመኑን አጠቃላይ ድምፅ ይወክላል፡፡
  • YeTimket LIjoch Besera layየዛሬው ውይይት፣ ይኸው ወጣት የበጎ ፈቃድ አገልጋይ በብቁ አመራር እየታገዘ ዐውቆትና ተገንዝቦት በቅድመ ግንባር የሚያስፈጽመውና በደጀንነት የሚደግፈው የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ኃያልነቱን የሚያረጋግጥበት ነው የሚኾነው፡፡ የተቋማዊ ለውጥ ንቅናቄው የሰላ ጫፍ ነውና የማይሻገረውና የማይጠራርገው ዕንቅፋት አይኖርም!!

No comments:

Post a Comment