Thursday, January 30, 2014

አዜብ መስፍን አኩርፋለች::...ጌታቸው አሰፋ ቆስሏል ተገሏል የሚል የሃሰት መረጃ እያሰራጨች ነው::"እነሱ ናቸው እንጂ የእኛን የሚያውቁት እኛ የነሱን ጉድ አናውቅም::"

Source:Minilik Salsawi
በሕወሓት ውስጥ የስልጣን እና የጡረታ ድልድል ይኖራል::የደብረጺሆን እና ጌታቸው አንጃ የትግራይ አንጃ ሕልውና ማንሰራራት አሳስቧቸዋል::አዜብ መስፍን አኩርፋለች::...ጌታቸው አሰፋ ቆስሏል ተገሏል የሚል የሃሰት መረጃ እያሰራጨች ነው:: "እነሱ ናቸው እንጂ የእኛን የሚያውቁት እኛ የነሱን ጉድ አናውቅም::"በደህንነት ቢሮ የብኣዴን ሰው የሕወሓት ውስጥ ከአንገት በላይ የተደረገው እርቅ ጥላቻ አገርሽቶ በደብረጺሆን እና በጌታቸው የሚመራው የአዲስ አበባው አንጃ / ሳሞራ የኑስን በማርሻል ማእረግ ከሰጠ በኋላ እንዲሁን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን አቶ በረከት ስምኦንን አባይ ወልዱን እና ስዩም መስፍንን ከአጠቃልይ የመንግስት ስራዎች ጡረታ ያወጣቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ እንዲሁም ስብሃት ነጋን እና እህቱን ቅዱሳን ነጋን ቴዎድሮስ ሃጎስን እና አዲስ አለም ባሌማን ነጻነት አስፋውን እና ተክለወይን አሰፋን ተወልደ አጋመን እና ብርሃነ ገብረክርስቶስን በተለያየ መንገድ በማሰናበት እና በሙስና በመያዝ ከድርጅቱ እንቅስቃሴ ሊያስወግዷቸው መሆኑን ምንጮች ለመቀለው አንጃ ጠቁመዋል::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የደብረጺሆን እና የጌታቸው ቡድን እርቁን ተከትሎ ውስጥ ውስጡን ያንሰራራውን የመቀሌውን ቡድን እና የመለስ አቀንቃኞች የሆኑትን ብትግራይ እና ከቀሪው የኢትዮጵያ ክልል በሙስና እና በተለያዩ የአፈጻሰም ችግሮች በሚል ለማስወገድ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል:: ይህንን ደርሰንበታል ያለው የመቀሌው ቡድን መረጃውን ተከትሎ አዲስ አበባ ውስጥ የደህንነት ሹሙ የሆነው ጌታቸው አሰፋ ማንነቱ ካልታወቀ ሰው በተቃታበት የመግደል ሙከራ በተተኮሰበት ጥይት እንደቆሰለ መረጃዎች ሽው እያሉ ነው እስካሁን ከታመነ ምንጭ ማረጋገጥ አልተቻለም::የሚል ዜና በማሰራጨት በሃሰት መረጃ የሕወሓትን ካድሬዎች ለመበጥበጥ መርዝ እየረጩ ነው ሲል የደብረጽዮን ቡድን አጣጥሎታል::ሆኖም እውነት ሊሆን ይችላል የሚሉ ምንጮች ቢገኙም ማስረጃ ማምጣት ግን አልቻሉም:: 

የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ይቀጥላል የሚለው የደብረጺሆን ቡድን የፖለቲካ ባላንጣዎቹን ለመጥለፍ እየተሯሯጠ ነው ሲሉ የመቀሌ አንጃዎች መክሰስ ጀምረዋል::ቀስ በቀስ እያባበሉ ሊያጸዱን ነው የሚሉት እነ አባይ ወልዱ አጥንታችንን እስር ቤት ውስጥ ሊቀብሩት ይችላሉ የሚል ስሞታ ማሰማት ጀምረዋል:: የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ሆነው በወያኔን ታማኝ አሽከር ተወዳዳሪያቸውን አሸንፈዋል የተባሉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን የቢዝነስ አጋሮቻቸው ታፍሰው በሙስና ወደ ወህኒ መወርወራቸውን ተከትሎ በማኩረፋቸው ወደ መንግስታዊም ይሁን ፓርቲያዊ ስብሰባ የግዴታ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር መተው የማያውቁ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ወደ ውጪ በመብረር እና በቢሯቸው በማሳለፍ እንደሚያጠፉ ሲታወቅ በአዲስ አበባው አንጃ ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ ይገኛሉ::

No comments:

Post a Comment