Sunday, January 19, 2014

‹‹ሕይወት አያሌውን የሚያቆም ማን ነው?››

ሠላሳ ሁለተኛው የአገር አቋራጭ ውድድር በስፔን ሴቪላ ከተማ በዕለተ ሰንበት (ጥር 11) ሲከናወን በሴቶች 8 ኪ.ሜ. ውድድር ኢትዮጵያዊቷን ‹‹ሕይወት አያሌውን ከማሸነፍ የሚያቆም ማን ነው?››
ብሎ የዘገበው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ድረ ገጽ ዘጋቢ ነው፡፡ ኢሜትሪዮ ቫሌንቴ እንደጻፈው፣ የ2013 የዓለም አገር አቋራጭ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ሕይወት በዛሬው ውድድር አምስተኛውን ተከታታይ የአገር አቋራጭ ድልን ለማጣጣም አልማለች፡፡ ዘንድሮ አራት ውድድሮችን በአታቸርካ (ኅዳር 8)፣ በሌፍሪንቦኬ (ኅዳር 15)፣ በሳንጆርጂዮ (ታኅሣሥ 28)፣ እና በኢልሳይባር (ጥር 4) አድርጋ በሁሉም አሸንፋለች፡፡ 
ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ተወዳዳሪ በዓለም ወጣቶች አገር አቋራጭ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ዓለሚቱ ሃሮዬ ስትሆን፣ በስፔን ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያቱ ረሂማ ጀዋርያና ትርሃስ ገብረ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ድረ ገጹ ዘግቧል፡፡ 

No comments:

Post a Comment