Tuesday, January 14, 2014

[የሳዑዲ ጉዳይ] – የማለዳ ወግ… የመረጃዎች እውነት፣ የውሸት ፍልሚያ ጅማሮ

 ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢ
የተመላሾች ጉዳይ …
በርካታ ከሳውዲ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል ። ”
safe_image-17
1604714_600436510028405_2111798139_n
1503996_745205042175145_1244234811_n
በግል ሃገር ግብተው የማገኛቸውን በርካቶች ሃገር ቤት ተመልሰው የጋጠማቸው የኑሮ ውድነት አማሯቸዋል። መልሶ ማቋቋሙ ደግሞ ከወሬ ባለፈ አለመጀመሩን እየሰማን ነው ። ባሳለፍነው እሁድ በጀርመን ራዲዮ እንዎያይ ፕሮግራም የቀረበው ተመላሽ ወንድምም ተመላሾችን በማደራጀቱና መልሶ በማቋቋሙ ረገድ የተጀመረ ነገር እንደ ሌለ መረጃውን አካፍሎናል። በአንጻሩ በመንግስት ኢቲቪና የቀሩት በስሩ የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃን የሚናገሩት የሚታመን ከሆነ “ተመላሾቹ በየክልሉ ተደራጅተው እራሳቸውን የሚያቋቁሙበት ስራ ተጀመሯል!” የሚል መልካም መረጃ እያስተላለፉ ይገኛሉ …ከዚህ ጋር ያያዝኩት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ” ከስደት ተመላሾች ሥልጠና ጀምረዋል !” በሚል ሁላችንም ሳውዲን ለቀን ወደ ሃገር እንገባ ዘንድ የሚያበረታታ መልካም የብስራት ዜና አሰራጭቷል። … እውነት ከሆነ ማለቴ ነው ! ይህንን አሻግሮ ተቀምጦ “እውንት እውሸት “ማለት አይቻልምና ሊናገሩ የሚገባቸው ባለቤቶቹ ብቻ ናቸው ። ተመላሾች ሆይ ምን ትላላችሁ?
አለም አቀፉ የስደተኞች ተጠሪ IOM መስሪያ ቤት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም $13.1 ሚሊዮን ዶላር ወይም 9.5 ዩሮ እንደሚያስፈልግ ይፋ አድርጓል ። የስደተኞች ንብረት በተለይ የሻንጣ ጌጣጌጡን መጥፋት ጉዳይ አሳሳቢነት ግን ከፍተኛ ሃላፊዎችን ሳይቀር ያስደመመ እንደሆነ በሚሰራጩት መረጃዎች ለመረዳት አልገደደንም ።
“ወደ ሃገር ግቡ አንገባም ፣ እንግባ አትገቡም …”
ከአሰሪያቸው ጋር የማይሰሩና በህገ ወጥነት የተፈረጁ ዜጎች ወደ ሃገር እንዲመለሱ የሚጠይቀው የሳውዲ መንግስትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንባሲና የቆንስል መስሪያ ቤቶች ጥሪ ነው። ጥሪው በቀጥታ የሚመለከታቸው ሰነዳቸውን ያላሟሉ የሚባሉት በባህር በኡምራና ሃጅ ብቻ ሳይሆን በስራ ኮንትራት መጥተው ከአሰሪዎቻቸው ጋር የማይሰሩ “ህገ ወጥ ” የተባሉ ዜጎች ግን “ሳውዲን ለቃችሁ ውጡ! ” የሚለውን ጥሪ ችላ በማለት ዘና ብለው የተለመደ ኑሯቸውን መኖር ጀምረዋል። ፍርሃትና ጭንቀቱ የት እንደገባ ባይታወቅም የሳውዲ መንግስት ባሳለፍነው ሳምንት ጉዳያቸውን ጀምረው ላልጨረሱ የሰጠው የሁለት ወር ማስተካከያ ጊዜ ገደብ ነዋሪውን ያዘናጋው ይመስላል። ያን ሰሞን በስጋት እቃቸውን ሲጠራርፉ የነበሩት ዛሬ እቃቸውን ወደ ነበረበት መልሰው የለመዱትን የመዘናጋት ኑሮ መግፋት ይዘዋል። አንዳንዶቹን ጠይቄያቸው “ዛሬም የሳውዲ መንግስት አይጨክንም ህጉን ያሻሽለዋል!” በማለት ሲመልሱልኝ አንዳንዶቹ ደግሞ “ሃገር ቤት የሄዱት የኑሮ ውድነት እያማረራቸው እየሰማን መሄዱ ማበድ ነው “ሲሉ መልሰውልኛል። እስርና ቅጣቱስ አልኳቸው እንዴት ትቋቋሙት አላችሁ? አልኳቸው “የፈለገው ቢሆን እዚሁ ሁኔ መቋቋም እና መቀበሉ ይቀላል!” ሲሉ ክችም ያለ መልስ ሰጥተውኛል! እኒህ ለእኔ ቀቢጸ ተስፈኞች ናቸው ..
የሳውዲን መንግስት ወደፊት ጠንከር ብሎ ይወስደዋል ተብሎ የሚጠበቀውን እርምጃ የፈሩ ጥቂቶች አሁንም ወደ መጠለያ በመግባት እና ለመግባት በዝግጅት ላይ ናቸው። ያም ሆኖ በጅዳ የሽሜሲ መጠለያ ሰነዳቸው ይሰራላቸው ዘንድ በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ በስልክ እየደወሉ “ተቸገርን። የምግቡ ችግር ቢቻልም፣ በመጓጓዙ ላይ ዘገየን፣ መላ ወደሚገኝበት ቦታ ጩኸልን !” እያሉ ተማጽነውኛል ። ትናንት ሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት መረጃ ያቀበሉኝ “ከመዲናና ከጅዳና ከተለያዩ ቦታወች ከቀናትና ከሳምንታት እና ከወር በፊት ወደ ሽሜሲ ገባን!” ያሉኝ ወገኖች “ጉዟችን ለማፋጠን በቆንስላችን ክትትልና ትብብር ስለማይደረግልን እየተጉላላን ነው !” ሲሉ ጭንቀታቸውን ገልጸውልኛል። በኮንትራት ስራ የመጡትን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ችግሩ መቋጫ አግኝቷል ቢባልም አሁን ድረስ ችግሩ አለመፈታቱን ነዋሪዎች ከሽሜሲ መጠለያ በምሬት ገልጸውልኛል። “ካለፉት …read more
Source: Zehabesha

No comments:

Post a Comment