Monday, January 20, 2014

በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኙ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ መሆናቸው ከዩንቨርስቲው የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣

በመረጃው መሰረት ከደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች በታህሳስ 29/2006 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በስለት ተገድለው መገኘታቸውና። ከነዚህም።- ፍሮምሳ ሃይለስላሴ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅና ግርማቸው መኳንንት የአማራ ብሄር ተወላጅ እንደሆኑ ተገልፅዋል፣፣
    መረጃው በማስከተል በዩንቨርስቲው ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ባለው ግድያ በከባድ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ምክንያት፣ትምህርታቸውን በአግባብ እንዳይከታተሉ በማሸማቅቅ ላይ እንደሚገኙና፣ቤተሰቦቻቸውም ትልቅ ስጋት ላይ መውደቃቸውን መረጃው አስረድትዋል፣፣
      በተመሳሳይ ሁኔታ በጎንደር አካባቢ ማክሰኞት በተባለች ከተማ አንድ የታጠቀ ወታደር። የሺ ተሻገር፤ ለተባለች የሆቴልዋ ባለቤት በሃይል ለመድፈር በሞከረበት ግዜ ባሰማችው የእርዱኝ ጩኸት። በወቅቱ ለመርዳት ለመጡ   አቶ መንግስቱ፤ የሆቴሉን ዘበኛ ኣቶ ዳኛቸው አለባቸውንና የሆቴሉን ባለቤት ለሆነችው ግለ ሰብ። ቦንብ አፈንድቶ ገድልዋቸው እንደተሰወረ ለማወቅ ተችልዋል፣
    ግድያው በተፈፀመበት ወቅት በመዋቾች ቤተሰብና ባአካባቢው ህብረተሰብ ከባድ ግርግር በመከሰቱ ምክንያትም። በንፁሃኑ ወገኖች ላይ እሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ኣካል ሳይያዝ ማምለጡ ያካባቢው የፀጥታና ያስተዳደር ድክመት ውጤት ነው ብለው እየገለፁ መሆናቸው ታውቀዋል፣፣
Source:http://demhitonline.blogspot.no/

No comments:

Post a Comment