Friday, January 17, 2014

በደቡብ ክልል 60 አቃቢ ህጎች ከስራ መባረራቸው ተሰማ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህጎቹ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ መባረራቸው ተግልጿል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እንደገለጹት ከ100 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ የተለያዩ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ወስደዋል። ከ40 በላይ በሚሆኑ የእስር ቤቶች ሃላፊዎች ላይም እንዲሁ የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን 10 ከስራ ተባረዋል።

ጉቦ መቀበል፣ ወገናዊነት፣ ፍትህ ማዛባት እንዲሁም እስረኞችን እየፈቱ መልቀቅ ከዋና ዋና ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። የኢሳት የደቡብ ክልል ዘጋቢ እንደሚለው ግን እርምጃው የተወሰደው የክልሉ መንግስት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ነው። በተለያዩ ወረዳዎች በተደረጉት ግምገማዎች የመንግስትን አሰራር አይደግፉም የተባሉ ሰዎች እንዲነሱ መደረጉንም ዘጋቢያችን ገልጿል።
Source: Ethsat

No comments:

Post a Comment