Thursday, January 23, 2014

በቦረና ኦሮሞና በቡርጂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ተሰደዱ


ከዚህ ቀደም በቦረና በተደረገ ግጭት የተነሳ ፎቶ ነው (ፎቶ ከፋይል)

ከዚህ ቀደም በቦረና በተደረገ ግጭት የተነሳ ፎቶ ነው (ፎቶ ከፋይል)
(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው) ቦረና አከባቢ የሚኖሩ ቡርጂዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የግጭቱ መንስኤ በቡርጂ መንደር ተገድሎ ተገኘ ተባለ የቦረና ብሄረሰብ አባል አስከሬን ነው፡፡ ባለፉት 70 እና 80 ዓመታት በዚያ አከባቢ ከመኖራቸውም በላይ የኦሮሚኛ ተናጋሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቡርጂዎች ዛሬ ለመፈናቀል ያበቃቸው ምክንያት ሴራ እንሆነ ይናገራሉ፡፡ እንደአስተያየት ሰጪዎች መረጃ ታህሳስ 25 በድሬ ወረዳ ሜጋ ከተማ የቡርጂ ተወላጅ ተማሪዎች ክፍል እንዳይገቡ ተከለከሉ፡፡ በ27/ 04 /2006 ዓ.ም በቦዳ ጫጩ ሩምሴ ቀበሌ አቶ ጃርሶ ተባለ የቦረና አባል ሁን ተብሎ በካድሬዎች የግጭት መንስኤ እንዲሆን የተቀነባበረ ሴራ ተገድሎ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ በዚሁ እለት በቦዳ ዜሮ ቀበሌ አቶ ገልገሎ ሁቃ የተባለ የበረና አባል ተገድሎ ተገኘ ፡፡ በዚሁ ግጭት ጫልሰሞ ጮልጎ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባል በኢታኔ ገልዶ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ሱማሌ ህርቦ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ ደግሞ በቦዳ ዜሮ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ቦዴ ፊርጤ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባልም ተገደሉ፡፡
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የቡርጂ ሰዎች
1. አቶ ጉዮ ሞሉ
2. አቶ እብቻ ሎሌ
3. አቶ ብሩ አሸቱ
ቡርጂዎች ይህንን ተከትሎ
1. ቦዳ ዜሮ ቀበሌ
2. ቡላዳ ቀበሌ
3. ዲደ ሜጋ ቀበሌ
4. ኦላ ሰፋ መንደር ተፈናቀሉ ሲሆን በሜጋ ከተማ የህዝብ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በግጭቱ የተነሳ ከአንድ ሺህ በላይ ቡርጂዎች መሰደዳቸው ታውቋል፡፡
Ze-Habesha Website

No comments:

Post a Comment