Tuesday, February 25, 2014

በህዝባዊ ሰልፉ ለኦሰካር ሽልማት ከታጨው አደባባይ ምን እንማር

ከአዲስ አበባ ወጣ ስንልም ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ወይም ተቃውሞን የሚገልጽባቸው አደባባዮች ሞልተዋል። የሚቃወመዉም ሆነ የሚደግፈው ሰው ግን ከዛ ቦታ የሚገኘው ለ አንድ ቀን ለዛውም ለሰልፉ በተፈቀዱት ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው። የመስቀል ደመራ ተደምሮ እሳቱን ለኩሶ እጣኑን አጭሶ ጸሎቱ ሰማይ ይድረስ አይድረስ ሳያረጋግጥ ተቃጥሎ ሳያልቅ ደመራው ወዴት እንደወደቀ ሳያይ እሽቅድምድሙ ቶሎ ቤት ለመግባት ነው። ይህን በዩኔስኮ በ አለም ቅርስነት የተመዘገበ የመስቀል ደመራ በዓል ለማነፃፀሪያ ተጠቀሰ እንጂ በዚህ ጽሁፍ ለመጠየቅ የምፈልገው የፖለቲካ ጥያቄን ህዝቡ ለመጠየቅ ተሰብስቦ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሽ ሳያገኝ አደባባዩን ለምን ሰው ይለቃል ለማለት ነው።

Source: Ecadforum

No comments:

Post a Comment