Wednesday, February 26, 2014

የአሜሪካዋ አሪዞና ግዛት ነጋዴዎች ለግብረ ሰዶማውያን አገልግሎት ያለመስጠት መብታቸውን በሕግ አስከበረች።

ሪዞና ክፍለሀገር ገዢ ጃን ብሬወር

የአሜሪካዋ አሪዞና ክፍለሀገር ገዢ ጃን ብሬወር ዛሬ እንዳስታወቁት የኃይማኖት ነፃነት የሚፈቅደው ሕግ ሥራ ላይ እንደሚውል እና ማንኛውም አገልግሎት ሰጭም ሆነ የሸቀጥ አቅራቢ አገልግሎቱን ለግብረ ሰዶማውያን አልሰጥም የማለት መብቱ ተረጋግጧል።ሕጉ በሥራ ላይ መዋሉን የአሪዞና ክፍለ ሀገር ገዢ በቀጥታ ስርጭት ሲያስታውቁ ህዝቡ ደስታውን በጭፈራ ገልጧል።
ለግብረ ሰዶማውያን እውቅና በመስጠት የምትታወቀው አሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕጉን በሀገራቸው እንዳይሰራ ያደረጉትን ሃገራት ስትወርፍ እና ማስጠንቀቅያ ስትሰጥ ሰንብታለች።በአፍሪካ ፀረ-ግብረ ሰዶማዊነት ሕግን በቅርቡ ያፀደቀችው ዑጋንዳ ከአሜሪካ ዛቻ ሲዘነበርባት መክረሙ ይታወቃል።በአለም ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛው ሀገሮች ግብረ-ሰዶማዊነት በሕግ የታገደ ነው።ሆኖም ግን ግብሩን በትምህርት ቤቶች እና ሰዋራ ቦታዎች ላይ በድብቅ እየተስፋፋ መሆኑን አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ።
ጥናቶቹ ግብረ-ሰዶም በወቅቱ ካልተገታ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ችግር የሚያሳይ ቢሆንም መንግስት ግን ምንም እርምጃ ካለመውሰዱም በላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዙ የተደርጉ አለም አቀፍ ተብዬ ስብሰባዎችን የሃይማኖት አባቶች እንዳይቃወሙ መከልከሉ ይታወሳል።ከእዚህ በተጨማሪ የሴቶች፣ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ዘነቡ በትዊተር ገፃቸው ለቀቁት የተባለው አሳፋሪ አባባል ብዙ ኢትዮጵያንን ያሳዘነ ሆኗል።
የአሜሪካ ክፍለ ሃገራት
አሜሪካ ለሰው ልጆች መብት እቆማለሁ እያለች የአዚህ አይነቱን ህብረተሰብ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠውን ከተቃራኒ ፆታ ጋብቻ ውጭ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በቀረው አለም ላይ እንደ ርዕዮተ አለም ለመጫን መሞከሯ እጅግ አስተዛዛቢ አድርጎታል።የዛሬው የአሪዞና ክፍለሀገር ገዢ ገለፃ ደግሞ አሜሪካ በሀገሯ ያለውን ሕዝብ በኃይል ይዛ ነው እንዴ ለሌላው ጠበቃ የሆነችው? አሰኝቷል።በመጨረሻም የግብረ ሰዶማዊነትን ተግባር የማትቀበለው እና በሕግ የምትቃወመው የሩስያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአሜሪካኖች በተናገሩት ንግግር ሃሳቤን ልደምድም። ”የግብረ ሰዶም ተግባርን በሩስያ ላይ ለመጫን አትሞክሩ።የሩስያ ሕብረተሰብ ዋጋ የሚሰጣቸው እሴቶቹ ሊከበሩ ይገባል።ቢያንስ ምንም የማያውቁትን ሕፃናት ተዉአቸው በነፃ ይደጉበት” ነበር ያሉት።
Source: gudayachn

No comments:

Post a Comment